Prosperity Party

የአስተዳደር ወረዳ ብልጽግና የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች ኮንፍረንስ ተካሄደ


የአስተዳደር ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የ2018 የስድስት ወራት የፓርቲ ሥራዎች አፈፃፀም ኮንፈረንስ አካሂዷል። 

በመርሀግብሩ ላይ የአስተዳደር ክላስተር ሰብሳቢ ክቡር አቶ መለሰ አለሙ፣ የአስተዳደር ብልጽግና ወረዳ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ፣ የአስተዳደር ብልጽግና ወረዳ ም/ሰብሳቢ ክቡር ዶ/ር አክሊሉ ታደሰ፣ ሌሎች የክላስተር እና የወረዳ አመራሮችና አባላት ተገኝተዋል፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳና የአስተዳደር ክላስተር ሰብሳቢ ክቡር አቶ መለሰ ዓለሙ ባስተላለፉት መልዕክት በዚህም የአስተዳደር ወረዳ እየሠራ ያለው ሥራ አመርቂ የሆነ፣ በህብረቶች መካከል ጥሩ ፉክክር እንዳለና ከሌሎቹም ወረዳዎች ጋር የፉክክርና የትብብር መንፈስ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ 

ከምርጫ ጋር አያይዘው ባስተላለፉት መልዕክትም አመራሩና አባላት በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ወቅትና ከምርጫ በኋላ ማከናወን ያለባቸውን ድርጊቶች ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ 

የአስተዳደር ብልጽግና ወረዳ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ አለምፀሐይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት፤ በባለፉት ስድስት ወራት የፓርቲ ሥራዎች አፈፃፀም በአመርቂ ሁኔታ መፈፀማቸውና ለዚህም ስኬት ርብርብ ላደረጉ በየደረጃው ላሉ አመራሮችና አባላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡  

የቀሪ ስድስት ወራት የፓርቲ ሥራዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሠረት እንዲከናወኑ በተለይም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ከማዕከል የሚወርዱትን የምርጫ ማስፈፀሚያ አቅጣጫዎችን ትኩረት በማድረግ የወረዳው አመራርና አባላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ 

የወረዳው የስድስት ወራት የፓርቲ ሥራዎች አፈፃፀም ሪፖርትና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እንዲሁም  የሥነ-ምግባርና ኢንስፔክሽን የስድስት ወራት ግኝቶች ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ 

የተሸለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ህብረቶች የእውቅና መርሃ-ግብር ተካሂዷል፡፡

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party