Prosperity Party

ምርጫ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መሰረት የሚጣልበት፣ የህዝብ ሉዓላዊነት የሚረጋገጥበት ነዉ- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ //ቤት 7ኛው ሀገራዊና ከተማ አቀፍ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ ፕሮግራም በዛሬዉ እለት አካሂዷል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፤ ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ መሰረት የሚጣልበት እንዲሁም የህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት የሚረጋገጥበት ስርዓት እንደመሆኑበ ሰላማዊ፣ ፍትሀዊ እና ዴሞክርሲያዊ መልኩ እንዲካሄድ ለማስቻል ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ጥንታዊ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት እሴቶች ያሏት ታላቅ ሀገር ብትሆንም በብዙ መልኩ የዓለም ጭራ ሆና የቆየችው የህዝብ ሉዓላዊነት እና የሀሳብ የበላይነት ሳይከበር በመቆየቱ መሆኑን ያስገነዘቡት ክብርት ከንቲባ፤ ሃገራችን ትናንትን እያከመች ነገን እየተለመች ወደ ፊት እየተጓዘች እንደምትገኝ አስረድተዋል።

2013 . ላይ የተካሄደዉ 6ኛዉ ሃገራዊ ምርጫ ህዝባችን በድምፁ መንግስት የመመስረት ሉዓላዊ ስልጣኑን በአግባቡ የተጠቀመበት እንደነበር ያወሱት ወ/ር አዳነች ባለፈዉ ምርጫ ወቅት የተጣለውን መሰረት ይበልጥ በማፅናት ዴሞክራሲን ለመገንባት 7ኛው ከተማ አቀፍና ሀገራዊ ምርጫ ሙሉ ዝግጅት እንደተደረገም ተናግረዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ //ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በበኩላቸው፤ ሀገር በቀል በሆነው የመደመር እሳቤ የሚመራው ብልፅግና ፓርቲ በቃሉ በመታመን ሀገራዊ ድሎችን ማስመዝገቡን ጠቅሰው የከተማችን ስምና ግብር በማገናኘት በተመዘገበው አንፀባራቂ ስኬት የህዝባችን እምነት መለምለሙን አስረድተዋል።

አዲስ አበባ ከሁሉም በሁሉም ለሁሉም መሆኗን  ያረጋገጡ ዘርፈ ብዙ ውጤቶች መመዝገባቸውን የገለፁት አቶ ሞገስ

ሀገራዊ የማንሰራራት ጉዞው  እንዲሁም የአዲስ አበባ የብልፅግና ተምሳሌትነት ተጠናክሮ መቀጠሉን አስገንዝበዋል።

በያዝነው ዓመት ከተማችንም ሀገራችንም ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበጥ ብርሃን መሸጋገራቸውን ያወሱት ኃላፊው

ከተማችንንም ሀገራችንንም የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የተቀመጠው ግልፅ ራዕይ ዕውን እንዲሆን በእሳቤዎች የተቃኘ በተግባራዊ ውጤታማነት የታጀበ ማኒፌስቶ በዛሬው ዕለት ይፋ መደረጉን ገልፀዋል።

በሁሉም መስክ አዲስ አበባ ፀጋዎቿን በማልማት የጠንካራ ሀገር ተምሳሌትነቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል የተመላከተ ሲሆን በትብብር እና በፉክክር መካከል ያለውን ሚዛን የሚጠብቅ በመግባባት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲ የመገንባት ርብርቡ ይበልጥ እንደሚጎለብት በፕሮግራሙ ላይ ተጠቅሷል።

በፕሮግራሙ ላይ የፓርቲያች ማኒፌስቶ ይፋ የተደረገ ሲሆን የመደመር የብልፅግና የልዕልና ትርጉም ያለው የብልፅግና ፓርቲ መለያ ምልክት የሆነው የስንዴ ነዶ በታላቅ ድምቀት ተዋውቋል።

ዛሬ የካቲት 9 / 2018 . በተካሄደው በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ //ቤት 7ኛው ሀገራዊና ከተማ አቀፍ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቅያ ፕሮግራም ከፍተኛ አመራሮች የፓርቲያችን አባላት ደጋፊዎች እና ልዩ ልዩ የህብረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party