ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባና ሌሎች ወረዳዎች በተከሠተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸው ላለፈ ዜጎች በስፍራው በመገኘት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት የሐዘን መግለጫ መልዕክት በጋሞ ዞን ጋጮ ባባና ሌሎች ወረዳዎች በበልግ ዝናብ ምክንያት በተከሠተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸው ላለፈ ዜጎቻችን የተሰማኝን ሐዘን እገልጻለሁ ብለዋል።
መንግሥት ለተጎጂ ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል ተገቢው ጥናትና ሥራ መከናወን አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፤ የጥንቃቄ ተግባራት አስፈላጊ መሆናቸውንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡