ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተነሱላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ:-
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተነሱላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ:-
⨳ ኢትዮጵያ ኤ አይን ስታስተዋውቅ ኤ አይን ያስተዋወቀ አንድም የአፍሪካ ሀገር አልነበረም፤ ነገም የእኛ የኤ አይ ዩኒቨርስቲን ለማቋቋም ቁልፍ የሆነ ጉዳያችን ነው፤ ታዳጊዎች ላይ አበክረን ከሰራን በቀጣይ በነገው አለም ላይ የሚወዳደሩ ትውልዶችን እንፈጥራለን።
⨳ በ2050 አብዛኛው የአለም ህዝብ ከተሜ ይሆናል በኢትዮጵያም በከተሜነት ግንባታ እየተገነባ ያለው የኮሪደር ልማት አሁን ብዙ ከተሞችን ነክቷል፤ በፕላን የተመራ ከተማን መፍጠር ከቻልን አሰተማማኝ ከተሜነትን ማረጋገጥ እንችላለን።
⨳ ባለፈው ዓመት በአለም ላይ 10 ፈጣን ዕድገት ከተመዘገባባቸው ሀገራት መካከል 5ቱ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው።
⨳ አይ ኤም ኤፍ አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሻለ ዕድገት ሊመዘገብ እንደሚችል እየተነበየ ነው።
⨳ ከአይ ኤም ኤፍ ከአንድ ፐርሰንት ያነሰ ትንበያን በዘንድሮ ማሳካት ተችሏል።