Prosperity Party

የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

 

ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በዋናው ጽ/ቤት በሚካሄደው መድረክ የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የዘርፍ ኃላፊዎች፣ የሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ሌሎች የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በመድረኩ በፓርቲውና በህዝብ ንቅናቄ የተሰሩ ስራዎች በጥልቀት እየተገመገመ የሚገኝ ሲሆን መድረኩም በሁሉም መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን ማስቀጠል እና ጉድለቶችን ለማረም የጋራ መግባባት ይፈጠራል።

በዛሬው የግምገማ መድረክ በዋናነት እንደ ፓርቲ በጋራ የታቀዱ ጉዳዮች አፈጻጸም የሚገመገም ሲሆን በበጀት ዓመቱ ትኩረት የሚሰጥባቸው ተግባራት ላይ ምክክር ይደረጋል።

የግምገማ መድረኩ በክልሎች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ የአፈጻጸም ወጥነት ለመፍጠርና እርስበርስ ለመማማር ያግዛል።

በተጨማሪም መድረኩ በሩብ ዓመቱ የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ለማስቀጠል እና የገጠሙን ችግሮች ላይ ተወያይቶ የጋራ መፍትሔ ለማፍለቅ የሚያግዝ ሲሆን በቀጣይ እርብርብ የምናደርግባቸውን መስኮች ለይቶ ለመስራት ይረዳል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party