Prosperity Party

የፓርቲ ህንፃዎች ለምረቃ መብቃት የአመራሩና የአባላቱን ትጋትና ቁርጠኝነት ያረጋግጣል - አቶ አደም ፋራህ

 

በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የፓርቲ አመራሮች ልዑካን ቡድን በሲዳማ ክልል የተገነቡ የፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንጻዎችን በዛሬና ነገ ይመርቃል፡፡

የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአባላቱና በህዝቡ ተሳትፎ በክልሉ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በሁሉም ዞኖች እና ወረዳዎች ያስገነባቸዉ 43 የፓርቲ ህንፃዎች ምርቃት መርሀ ግብር መከናወን ጀምሯል።

ህንጻዎቹን መርቀው ሥራ እያስጀመሩ ያሉት የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕረዚዳንትና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህና የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ናቸው።

የምረቃው ሥነሥርዓት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በዳካ ክ/ከተማ የተገነባውን የፓርቲውን ቅ/ጽ/ቤት ህንጻን በመመረቅ ተጀምሯል።

በዚሁ ወቅት የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እንደተናገሩት የፓርቲ ህንፃዎች ለምረቃ መብቃት የአመራሩና የአባላቱን ትጋትና ቁርጠኝነት ያረጋግጣል።

የህንፃዎቹ በጥራትና በፍጥነት መጠናቀቅ የሲዳማ ህዝብ ለፓርቲው ያለውን ፍቅርና የመደመር እሳቤዎች በአግባቡ ተግባራዊ መደረጋቸውንም ያረጋግጣል ብለዋል።

የሲዳማ ክልል በሁሉም የልማት ዘርፎች ግንባር ቀደም መሆኑንና በቤተሰብ ብልፅግና ሥራዎች በተለየ ብቃት እየሠራ መሆኑን የገለጹት አቶ አደም ፋራህ የህንጻ ግንባታውን በብቃት ማሳካት ስለቻላችሁ አመሠግናለሁ ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በበኩላቸዉ እንደገለፁት የብልጽግና ፓርቲ ባስቀመጠው መሠረት የህንፃ ግንባታው በስከት መሠራቱን አሳስበዉ ክልሉ በጠንካራ የልማት ጎዳና ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይነት በሲዳማ ክልል በሁሉም ዞኖች ሥር ያሉ በወረዳ ማዕከላት የተገነቡ የፓርቲው ቅ/ጽ/ቤት ህንጻዎችን መርቀዉ ሥራ የሚያስጀምሩ ይሆናል።

በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ የብልጽግና ፓርቲ የዋና ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮች፤ የተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የሲዳማ ክልል አመራሮች ተገኝተዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party