የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ መካሄድ ጀመረ
ዛሬ ሀምሌ 7/2017 ዓ.ም የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ በድሬዳዋ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፤ የዋና ጽ/ቤትና የክልልና የከተማ አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤቶች አመራሮች ተገኝተዋል።
በመርሀግብሩ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ ሪፖርት፤ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ማጠቃለያ ሪፖርት እና የ2018 በጀት አመት መሪ ዕቅድ ሪፖርት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።