Prosperity Party

የብልፅግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፎችና መስኮች ስኬታማ ጉዞ እያደረገ ይገኛል - ክቡር አቶ አደም ፋራህ

 

የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀመረ

ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በዋናው ጽ/ቤት እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የዘርፍ ኃላፊዎች፣ የሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ሌሎች የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የሩብ ዓመቱን የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በንግግር የከፈቱት የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እንደገለፁት ፓርቲው በሁሉም ዘርፎችና መስኮች ስኬታማ ጉዞ እያደረገ ይገኛል።

ፓርቲውን ለስኬት ያበቁትን አምስት አንኳር ነጥቦችን አብራርተዋል።

ለኢትዮጵያና ለፓርቲያችን በሚመጥን መንገድ ከፍ ተደርጎ በመታቀዱ፤ በመደመር እሳቤ ሁሉንም አቅሞች ለመጠቀም ጥረት በመደረጉ፤ በፕራግማቲክ እይታ በየአካባቢው ያለውን ተግባራዊ እውነታ መሰረት በመደረጉ፤ በፍጥነትና በፈጠራ መርህ በመሰራቱና ፈተናን ወደ ዕድል የመቀየር መርህ መከተል በመቻሉ ፓርቲው ዘርፈ ብዙ ስኬቶችንና ድሎችን አስመዝግቧል ብለዋል።

በመድረኩ በፓርቲውና በህዝብ ንቅናቄ የተሰሩ ስራዎች በጥልቀት የሚገመገሙ ሲሆን በሁሉም መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን ማስቀጠል እና ጉድለቶችን ለማረም የጋራ መግባባት ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party