Prosperity Party

በጎ መሪ ከበጎ ሠሪ ጋር የተገናኙበት የሎጎ ሐይቅ ፕሮጀክት- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ቃልን በተግባር የመለወጥ ጥበብ የታየበት፣ የተራቆቱ ተራራዎች እና የሐይቅ ዳርቻዎች ወደ ወርቃማ የልማት መሬትነት የተቀየሩበት የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ዛሬ ተመርቋል። 

በምርቃቱ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንደገለጹት፣ ይህ ፕሮጀክት ተራ ግንባታ ሳይሆን "ያላመነን የሚከራከር፣ የተጠራጠረን የሚያፀና ቋሚ ምስክር ነው"። 

የሎጎ ሐይቅ ሪዞርትን ሲገልጹት፣ “የታሪክ ጸሐፊዎች ስለ ሐይቅ ሲጽፉ፣ 'ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፊት እና በኋላ’ ብለው እንዲከፍሉ የሚያደርግ ትልቅ ለውጥ ተመዝግቧል" ብለዋል። 

ይህ የሚያሳየው የመደመር መንግሥት የማይሠራውን ቃል እንደማይገባ እና የገባውንም ቃል ፈጽሞ እንደማይዘነጋ ነው። 

"ይህ ፕሮጀክት በጎ መሪ (መንግሥት) ከበጎ ሠሪ (ባለሀብት እና ማኅበረሰብ) ጋር ሲቀናጅ ሀገር በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዴት እንደምትለወጥ በተግባር ያሳየ የብልጽግናችን አዲስ ምዕራፍ ነው" ሲሉም ነው የገለጹት። 

ሎጎ ሐይቅ ዛሬ ላይ የቱሪስት መዳረሻ ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያውያን የሥራ ባህል እና የአንድነት ውጤት ሆኖ ከፍ ብሎ ይታያል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። 

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party