Prosperity Party

ሰላምን ማፅናት የተጀመረውን ልማት ማስቀጠል በየሴክተሩ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየትና በመፍታት የህዝብን እርካታ ማረጋገጥ ትኩረት የተሰጠባቸው ጉዳዮች ናቸው - አቶ ፍቃዱ ተሰማ

 

በፌዴራል ተቋማት አደረጃጀት የአስተዳደር ብልፅግና ክላስተር የ2017 በጀት ዓመት የፖለቲካና የአደረጃጀት ስራዎች አፈጻጸም የወረዳዎች የእውቅና መርሀግብር አካሂዷል።

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የፌዴራል ተቋማት አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በዚህ ወቅት እንደገለፁት ሰላምን ማፅናት፣ የተጀመረውን ልማት ማስቀጠል፣ በየሴክተሩ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየትና በመፍታት የህዝብን እርካታ ማረጋገጥ፣ ትኩረት የተሰጠባቸው ጉዳዮች ናቸው።

ጠንካራ ፓርቲ መፍጠር አደረጃጀቶችን ተፅዕኖ እንዲፈጥሩ ማድረግ ይገባልም ብለዋል።

የአባላት ምዘና በዴሞክራሲያዊ ትግል በመምራት የአባላት ጥራት ማሰጠበቅ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የብልፅግና ፓርቲ ም/ቤት አባል እና የአስተዳደር ክላስተር ሰብሳቢ አቶ መለሰ ዓለሙ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ በሁሉም መስኮች አዎንታዊ ውጤት መመዝገቡን አንስተው፤ በላቀ አፈፃፀም የኢኮኖሚ አቅምን በማሳደግ ውጤታማነትን ማረጋገጥ የሚጠበቅ መሆኑን ገልፀዋል።

በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን በላቀ ሁኔታ በማስቀጠል እንዲሁም ድክመቶችን የእቅድ አካል ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ዛሬ በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት በተካሄደው መርሀግብር የ2017 በጀት አመት የፖለቲካና አፈፃፀም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ወረዳዎች እውቅና ተሰጥቷል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party