አይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመረቀ
ኢትዮጵያ የአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በይፋ በመመረቅ፤ በኢነርጂ ዘርፉ ላይ አዲስ ታሪክ የጻፈ ታላቅ እጥፋት ማስመዝገቧን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት እንደገለጸው፤ ኢትዮጵያ የአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በይፋ በመመረቅ፤ በኢነርጂ ዘርፉ ላይ አዲስ ታሪክ የጻፈ ታላቅ እጥፋት አስመዝግባለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድም፤ ይህ ውጤት የታዳሽ ኃይል አማራጮቻችንን ለማስፋፋት የወሰድነው ወሳኝ እርምጃ ምልክት ነው ሲሉ እንዳስገለፁም አስታውቋል።
የተረጋጋ የኃይል አቅርቦት በቴክኖሎጂ ለሚመራ ኢኮኖሚ ዋነኛው የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ መጠን፤ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ያላትን ርዕይ ወደ ተግባር ለመለወጥ ቁርጠኛ ብቻ ሳትሆን ከፍ ያለ እና በቂ የመፈፀም አቅም ያላት መሆኑንም በተግባር አሳይቷል ብሏል።