Prosperity Party

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካነሷቸው ጥያቄዎች፡-

➡️ የዘንድሮ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሃዊና በመላ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተዓማኒ እንዲሆን እንዲሁም በጸጥታ ችግሮች ምክንያት እንዳይስተጓጓል በመንግሥት በኩል ምን እየተሰራ ነው?

➡️ በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ትልቅ ተስፋን የጫረ ቢሆንም አሁን ላይ በሕወሓት ቡድን ምክንያት በክልሉ ውስጥ ሥርዓት አልበኝነት እንዲነግስና የግጭት ድባብ እያንዣበበ ይገኛል፤ የክልሉ አሁናዊ የሰላም ሁኔታ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

➡️ የትግራይ ክልል በሀገራዊ ምክክር ሒደት ንቁ ተሳታፊ ለማድረግ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር በቅንጅት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ምንድን ናቸው?

➡️በሀገራዊ ምክክር ጠንካራ ሀገራዊ መግባባት ፈጥረን የሀገሪቱ መፃዒ ዕድልን ብሩህ እንድናደርግ ከመላው ኢትዮጵያውያንና ባለድርሻ አካላት ምን ይጠበቃል?

➡️ የስራ አጥነት ቁጥርን ለመቀነስ መንግሥት ምን እየሰራ ነው?

➡️ የብሄራዊ ጥቅም ጉዳዮቻችንን ለይተን በአንድነት እንድንቆም ለማድረግ በመንግሥት በኩል ምን እየተሰራ ይገኛል፣

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party