Prosperity Party

የኢትዮጵያ የብሪክስ ጉባዔ ተሳትፎ በአጠቃላይ ውጤታማ ነበር - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)


በብራዚል ሪዮ ዲ ጄኒሮ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባኤ የኢትዮጵያ ተሳትፎ በአጠቃላይ ውጤታማ ነበር አሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በብራዚል የብሪክስ 17ኛ ጉባዔ ቆይታን በተመለከተ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በማብራሪያቸው፤ የብሪክስ ጉባዔ ተሳትፎ በአጠቃላይ ውጤታማ ነበር ብለዋል።

ከጉባዔው ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የሚያጠናክሩ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በጉባዔው ላይ ትኩረት ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል አጠቃላይ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ አንዱ እንደሆነ ገልጸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመድረኩ ባቀረቡት ሀሳብ ዓለም ሁሉንም አካባቢ ማቀፍ እንደሚገባት አስገንዝበዋል ነው ያሉት።

በተለይም የአፍሪካ ድምጽና ተሳትፎ በሁሉም ተቋማት ዘንድ ሊረጋገጥ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ረዥም ታሪክ፣ ስልጣኔ፣ ብዝሃ ባህል ያላት መሆኗን አንስተው፤ ማህበራዊ ልማትን ለማሳደግ በትብብር መስራት እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ የደቡብ ለደቡብ ሀገራት ግንኙነቶችን መጠናከር እንዳለበት ማመላከታቸውን ገጸዋል።

እንዲሁም ጉባዔው የኢኮኖሚ እና ፋይናንስ ጉዳይ በተለይም አዲሱን የብሪክስ ልማት ባንክ የሚጠናከርበት እና ለየሀገራቱ ልማት ፈንድ የሚያደርግበት ሁኔታ ላይ የመከረ መሆኑን ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በማብራሪያቸው ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ አጠቃላይ ከነዚህ ሀገራት ጋር ባለው ትብብር ተጠቃሚ እየሆነች እንደምትገኝ ማረጋገጣቸውን አስረድተዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ  ያለውን ኢ-ፍትሀዊ የፋይናንስ እና የብድር አቅርቦት ለመታደግ እንደዚህ አይነት አማራጮች አስፈላጊ በመሆኗቸው ኢትዮጵያ ተግታ እንደምትሰራ መግለጻቸውን ተናግረዋል።

በዲጅታል እና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አስተዳደር ላይ ጉባዔው መምከሩን ገልጸው፤ ኢትዮጵያም የዲጂታል ዓለሙ ዕድል እና ስጋቶች እንዳሉት በመረዳት ዕድሎቹን ለማስፋትና ስጋቶችን ለመቀነስ በትብብር መስራት እንደሚያስፈግ ዕምነት እንዳላት በመድረኩ አቅርባለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከዚህ አኳያ ሰፊ ስራዎችን እየሰራች መሆኗን አንስተው፤ ከሀገራቱ ጋር በሚኖር ትብብርም ይሄንን ለማጠናከር ተግታ እንደምትሰራ አረጋግጠዋል።

ጉባዔው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ባደረገው ውይይት ኢትዮጵያ ለዓለም ምሳሌ የሚሆኑ ስራዎች በመስራት ከንግግር ባለፈ ወደ ተግባር ቀይራ እየሰራች እንደሆነ ለመድረኩ አቅርባለች።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party