Prosperity Party

የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንፃዎችን መረቁ

 

የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፤ ከሀረሪ ክልል ፕሬዚዳንት ኦርዲን በዲሪ፣ ከክልልና ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በመሆን በአመራሩ፣ በአባላትና በህዝብ ተሳትፎ የተሰሩ ዘጠኝ የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንፃዎችን መርቀዋል።

በዚህ ወቅት የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እንደተናገሩት የቀደምት ስልጣኔ ማዕከል፣ የሰላም፣ የመቻቻልና የፍቅር ተምሳሌት ሆና የቆየችው ሀረር ከለውጡ በፊት በነበረው የፖለቲካ አመራር ጉድለት ምክንያት ዕድገቷ ተሸርሽሯል ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ መመስረት የሀረሪ ክልልን ከኋልዮሽ ጉዞ ወደ ከፍታ ጉዞ ቀይሯል ሲሉ ገልፀዋል።

የብልፅግና ፓርቲ መመስረት በክልሉ የአመራር አንድነት እንዲጠናከር አስችሏል፤ ይህም የህዝቡን አንድነትና አብሮነት በማጠናከር ክልሉን ወደ ፈጣን የልማት ጎዳና አስገብቷል፤ ለሀገር ተሞክሮ የሚሆኑ የልማት ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

በተባበረ ክንድ በክልሉ በዘጠኙም ወረዳ የተሰሩ ህንፃዎች ለሌሎችም ተምሳሌት በሚሆን የፕሮጀክት አመራር ስርዓት ነው የተገነቡት ነው ያሉት።

የተመረቁ ህንፃዎች ፓርቲው በመፍጠንና መፍጠር መርህ ያቀዳቸውን ፕሮጀክቶች በፍጥነት፣ በጥራትና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ በመገንባት ለሌሎችም ተምሳሌት የሚሆን የፕሮጀክት አመራር ስርዓት እየተከተለ መሆኑን አመላካች መሆናቸውን አብራርተዋል።

የፓርቲ ህንፃዎችን ለመገንባት አመራሩ አባላቱና መላው የክልሉ ህዝብ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

የሀረሪ ክልል ፕሬዚዳንት ኦርዲን በዲሪ በበኩላቸው

የሀረሪ ክልል ህዝብ ለዘመናት ልማትና ዕድገት ተርቦ ኖሯል፤ ባለፉት የለውጥ አመታት ግን የህዝቡ የልማት ጥያቄዎች በአመራሩና በህዝቡ የላቀ ተሳትፎ ምላሽ አግኝቷል ብለዋል።

በዚህም በግብርና፣ በመሰረተ ልማት፣ በኮሪደር ልማት፣ በማህበራዊ ልማትና የክልሉን ገቢ ከማሳደግ አኳያ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።

ለጠንካራ ፓርቲ መሰረት የሚሆኑና የፓርቲን ሁለንተናዊ አቅም በአደረጃጀት የሚያጠናክሩ ጽ/ቤቶች በክልሉ ውስጥ ተገንብተዋል ያሉት የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፥ ህዝባችን ከጎናችን በመቆሙ ተቋማዊ መሰረት የሚያስይዙ ተቋማትን መገንባት ችለናል ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፤ የሀረሪ ክልል ፕሬዚዳንት ኦርዲን በዲሪን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች አዲስ በተመረቀው ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party