በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ማብራሪያ:-
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ማብራሪያ:-
⨳ በግብርናው 999 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ ችለናል።
⨳ ኦርጋኒክ ማዳበሪያዎችን የማምረት ስራው እየተለመዱ መምጣታቸው ለውጡን የሚደግፍ ነው።
⨳ በሀገር ውስጥ ማዳበሪያዎችን ማምረት ብቻ በቂ ስላልሆነ እያንዳንዱን መሬት ፈትሸን መሬቱ እንደሚፈልገው ልክ ለማቅረብ ጥናት ጀምረናል ይህን ማሳካት ከቻልን ከ7.3 በመቶ በላይ ዘርፉን ማሳደግ እንችላለን።
⨳ በዚህ 6 ወር የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች የሀይል አቅርቦት 16 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።
⨳ ከሶላር ኤክስፖርት ብቻ 900 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እናገኛለን
⨳ 30 በመቶ በማዕድን ዘርፉ ዕድገት ተመዝግቧል።
⨳ ኢትዮጵያ ከካሽ ወደ ሞባይል ዋሌት ማደጓ ትልቅ ለውጥ እና የሚታይ ዝላይ ነው።
⨳ የቱሪስት ፍሰቱ ጨምሯል አለም አቀፍ ስብሰባዎችን እያከናውንን ነው 10.2 በመቶ እድገት እናመጣለን፤ ጠንክረን ከሰራን ከዚህም በላይ እናስመዘግባለን።