ሀገራችን ብዙ ወንዞችንና ለኃይል ማመንጨት ምቹ የሆነ ሥነ ምኅዳርን የታደለች ናት....
ሀገራችን ብዙ ወንዞችንና ለኃይል ማመንጨት ምቹ የሆነ ሥነ ምኅዳርን የታደለች ናት፡፡ ነገር ግን በቂ ኃይል ማመንጨት ጉዳይ ከዉጭም ከዉስጥም ባሉ የተለያዩ ተግዳሮቶች ሳይሳካ ለብዙ ዘመናት ቆይቷል፡፡ በዓባይ ወንዝ ላይ የኃይል ማመንጫ ለመገንባት የወሰደብን ጊዜ ጥቂት የሚባል አለመሆኑ ለዚህ ምስክር ነዉ፡፡ ከዉጭ የተለያዩ ሀገራት ጥቅማችንን ይነካል በሚል በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለሕዳሴ ግድብ ሊገኝ ይችል የነበረ የዉጭ ገንዘብ እንዳናገኝ ለማድረግ የሚያደርጉት ሤራ ተሳክቶላቸዋል፡፡
- የመደመር መንግሥት ገጽ- 59