Prosperity Party

"የፓርቲያችንን የአሰራር ስርዓት በማዘመን ዲጂታል ብልፅግናን እውን ለማድረግ የሚያስችል የዲጂታላይዜሽን ስራ ተጀምሯል"- አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራር እና የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት በስትራቴጂክ ስራ አመራርና የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ አዘጋጅነት ለዋና ጽ/ቤትና ለቅ/ጽ/ቤቶች በERP አውቶሜሽን ዙሪያ በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ ሲሰጥ የቆየው  ስልጠና ተጠናቋል።

በስልጠና ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራርና የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር እንደተናገሩት የፓርቲያችንን የአሰራር ስርዓትን በማዘመን እና ዲጂታል ብልፅግና እውን እንዲሆን ወሳኝ ሚና ያለው ስልጠና ባለፉት አራት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ መቆየቱን በማንሳት ስልጠና ሲሰጥበት የቆየው ሲስተም የስትራቴጂክ ስራ አመራርና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ባለሙያዎች እውቀትና ልፋት የተገነባ መሆኑ፣ ተቋማዊ አቅማችንና የቴክኖሎጂ ባለቤትነታችን (Technology Ownership) ምን ያህል እያደገ መምጣቱን ያሳየ ነው ብለዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የተበሰረው የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ስኬታማ እንዲሆን የተቋማት የዲጂታላይዜሽን ስራን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ዲጂታል ብልፅግናን እውን ለማድረግ ወሳኝ ሚና ያለው ሲስተም ላይ ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል።

ክቡር አምባሳደር ሀሰን አክለው እንደገለጹት ስልጠናው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሬድፎክስ (RedFox) ካምፓኒ የቴክኒክ ስልጠናውን ከመስጠት ባለፈ ጠቅላላ የስልጠናውን ወጪ በልግስና ስፖንሰር በማድረግ ላሳየው አርአያነት ያለው አጋርነት እንዲሁም የሲዳማ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ለስልጠናው ስኬት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በማመስገን በቀጣይ በስልጠናው የተገኘውን እውቀት ወደ ተግባር መለወጥ እንደሚገባ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በበኩላቸው ስልጠናው ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር ለምታደርገው ጉዞ ትልቅ መሰረት የሚጥል እንደሆነ በማንሳት የዲጂታላይዜሽን ትግበራ እውን እንዲሆን ፓርቲው የጀመረው ስራ የሚበረታታ መሆኑን በመግለጽ የፓርቲውን የሰው እና የገንዘብ ሀብት በቴክኖሎጂ በታገዘ ሁኔታ በማልማት ጠንካራ የፓርቲ የመገንባት ሂደት ስኬታማ እንዲሆን ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ በነበራቸው ቆይታ ያገኙት የተግባር እና የተሞክሮ እውቀቶችን በማስፋት ሌት ተቀን በትጋት በመስራት ዲጂታል ብልፅግናን እውን ለማድረግ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አቶ አብርሃም ገልጸዋል።

የሬድፎክስ (RedFox) ካምፓኒ ተወካይ ወ/ሪት ሊዲያ ዮናታን ሀገራችን ኢትዮጵያ በዲጂታላይዜሽን እና አውቶሜሽን ስራ ለምታደርገው የለውጥ ጉዞ ላይ ካምፓኒው በአጋርነት እየሰራ እንደሚገኝ እና ይህንን አጋርነት አጠናክሮ ለመቀጠል እንደሚሰራ አንስተዋል።

ስልጠናው የሀብት አጠቃቀም ሂደት በማዘመን፣ የተሳለጠ የመረጃ ልውውጥ ተግባራዊ በማድረግ የዲጂታልአይዜሽን ትግበራ በማስረጽ ረገድ ትልቅ ሚና ያለው የነበረው እንደነበር በስልጠና ተሳታፊዎች ተገልጿል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party