Prosperity Party

ዲጂታል ብልፅግናን እውን ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች አበረታች ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ

ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም

በብልፅግና ፓርቲ ዋና /ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራርና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ አዘጋጅነት ለዋና /ቤትና ለቅ//ቤቶች አመራሮችና ባለሙያዎች በተቀናጀ የተቋም ሀብት አስተዳደር ትግበራ ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ተጀምሯል።

በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ እየተሰጠ የሚገኘው ይህ ስልጠና፤ ብልፅግና ፓርቲ የጀመረውን የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ ተግባራዊ በማድረግ የፓርቲውን ተቋማዊ ጥንካሬ ለማስቀጠል የሚያግዝ ተግባር ተኮር ስልጠና ነው።

በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሲዳማ ክልል ሥራ፣ ክህሎት እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል / ሀገረፅዮን አበበ እንደተናገሩት ብልፅግና ፓርቲ የሀገራችንን ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት ከጀመራቸው ተግባራት መካከል የዲጂታላይዜሽን ስራ አንዱ እና ዋነኛው መሆኑን በመግለጽ  ብልፅግና ፓርቲ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የተያዙ ግቦች እንዲሳኩ በፓርቲው ለሰው ኃይል ግንባት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ትግበራ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት፣ ምቹ የአሰራር ሥርዓቶችን በመዘርጋትና የሰው ኃይሉን በማብቃት ረገድ ውጤታማ ሥራ መሰራቱንም አስታውሰዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ዋና /ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራርና የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዋና ባለሙያ የሆኑት አቶ ጌትነት ሙላት በበኩላቸዉ፤ ስልጠናው በየደረጃው ያሉ የፓርቲው መዋቅሮች ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ወጥ የአሰራር ሥርዓትን እንዲዘረጉ ያግዛል ብለዋል።

የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ //ቤት ስትራቴጂክ ስራ አመራርና የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታምሩ ዩቴ እንደተናገሩት፤ ብልፅግና ፓርቲ ዘመናዊ የሆነ እና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት አንዱ አካል የሆነው ERP አውቶሜሽን ስራ አንዱ አካል መሆኑን በማንሳት ለፓርቲው ተቋማዊ ግንባታ ጥንካሬ ወሳኝ ሚና ያለው ስልጠና መሆኑን አንስተዋል።

በስልጠናው ላይ ከዋና /ቤትና ከቅ//ቤቶች የተወጣጡ የስትራቴጂክ ስራ አመራርና የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ እንዲሁም የሀብት አስተዳደር ዘርፍ አመራሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት የሚቀጥል እንደሆነም ተገለፃል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party