የኢትዮጵያ ሴት ከፍተኛ አመራሮች በሕንድ የስልጠና እና የልምድ ልውውጥ አካሄዱ
የህንድ ጠቅላይ ሚንስትር ባሳለፍነው ወር በኢትዮጲያ ይፋዊና ታሪካዊ ጉብኝት ባደረጉበት ማግስት በተደረሰ የሁለትዮሽ የዲፕሎማሲ ስምምነት ለሴት አመራሮች የስልጠና ፣የልምድ ልዉዉጥ እና የጉብኝት መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተለይም ደግሞ በህብረት ስራ ማህበር በመደራጀት ከትንሽ ተነሰተዉ ትልልቅ ተቋማትንና ፋብሪካዎችን በመገንባት የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ፤ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር እንዲሁም የአገር ውስጥ የማምረት አቅምን በማዳበር ለአገራዊ እድገት እያበረከቱት ባለው አስተዋጽኦ ላይ ልምድ ልውውጥ ለማድረግና ተሞክሮ ለመቅሰም እና የኢትዮጵያና የህንድ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው፡፡
በስልጠናው እየተሳተፍ ያሉ ሴት አመራሮች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 ህንድ ሀገር በሚገኘው የኢትዮጲያ ኤምባሲ ጋር በድምቀት አክብረዋል።
የሉዑካን ቡድን የመሩት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሜ በዶ በመርሃ ግብሩ እንደገለጹት የሴቶች ቀን በሁሉም ዘርፍ ከዚህ ቀደም የነበሩ የተሳትፎና ተጠቃሚነት ጉድለቶች መታረማቸውንና ለውጥ መምጣቱን እየፈተሹ ለመሄድ ያግዛል ብለዋል። የሴቶችን አቅም ለማጎልበትና ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማረጋገጥ ከለውጡ ወዲህ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በፕሮግራሙ ተገኝተዉ የእንኳን መጣቹሁና እንኳን አደረሳቹሁ መልዕክት ያስተላለፍት በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ሞላልኝ አስፋዉ የሴቶች ቀን ሁሌም ቀናቸዉ ቢሆንም ለይቶ መከበር ያስፈለገበት ምክንያት ኦዲት ለማድረግ በዘርፍ ምን ተሰርቷል፤ ምን ይጎድለናል የሚለዉን በመፈተሽ የተሻለ ለመሰራት መሆኑን ጠቅሰዉ በኢንባሲዉ እሄን ፕሮግራም ከመጡ ከፍተኛ ሴት አመራሮች ጋር መከበሩ ትልቅ ትርጉም እንደሚሰጡት ገልፀዋል ።
በመድረኩ ከኢፈዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍና ከተለያዩ ሴት አደረጃጀት የተውጣጡ ሴት አመራሮች እየተሳተፍ ይገኛሉ፡፡
የዘንድሮው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን/ማርች 8 / በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ “50 ዓመት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነት እና ለበለፀገች ኢትዮጵያ'' በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ ይገኛል።