Prosperity Party

የብልጽግና ፓርቲ የ7ኛዉ ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ መወዳደሪያ ምልክትና ማኒፌስቶ ይፋ ማድረጊያ ስነስርዓት እየተካሄደ ነዉ

ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሄደው 7ኛ ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ የሚወዳደርበትን የምርጫ ምልክትና የምርጫ ማኒፌስቶ ለህዝብ ይፋ አድርጓል።  

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አደም ፋራህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመራር አባላት በመድረኩ ተገኝተዋል። 

ብልጽግና ፓርቲ ለ7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ የሚወዳደርበት ምልክት "የስንዴ ነዶ" ሲሆን: "ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር" የምርጫው መሪ መልዕክትነት እንደተሰየመም በመድረኩ ተገልጿል፡፡

የስንዴ ነዶ የመደመር፣ የአንድነትና የትብብር ተምሳሌትነትን የሚወክልና የምርታማነት መገለጫ እንደሆነም ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ 

የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመጪው ግንቦት 24/2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳወቁ ይታወሳል።

 

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party