Prosperity Party

የሰባተኛውን አገራዊ ምርጫ መንትያ ግቦችን ለማሳካት የብልፅግና ወረዳ አመራርና አባላት ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው- የብልፅግና ወረዳ ሰብሳቢ ወ/ሮ መስከረም አበበ

 የብልፅግና ወረዳ "ውጤታማ ምርጫ ለተምሳሌት አገር" በሚል መሪ ቃል የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው የስድስት ወር ግምገማ ኮንፈረንስ እያካሄደ ይገኛል፡፡ 

የብልፅግና ወረዳ ሰብሳቢና የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ም/ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መስከረም አበበ  በዚህ ወቅት እንደገለጹት በዓመቱ በፓርቲያችን መሪነት በፓለቲካ፣ ማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በዲፕሎማሲው ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት እና የብልጽግና ደማቅ አሻራዎች ማስቀመጥ የተቻለበት ነው፡፡

ከሁሉም በሁሉም ልቆ መገኘት በሚል መሪ ቃል እንደ ወረዳ ሲሰራ መቆየቱን ያነሱት ሰብሳቢዋ ከተቀመጠው ግብ አኳያ ፈጻሚ አካል ለይቶ እቅድ በማቅድ በፓለቲካ፣ በአደረጃጀትና በበጎ ፈቃድ ስራዎች ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል፡፡ 

ጎድለቶችን ለማረምና ልቆ ለመገኘት የሚያስችሉ የአቻ ለአቻ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በሕብረቶች ውስጥ እርስ በእርስ የመመማርና ተሞክሮ መለዋወጥ መቻሉ የተስተዋሉ ጉድቶችን በማረም አቅም እየፈጠሩ መጓዝ የተቻለበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በፌደራል ተቋማት አደረጃጀት የአስተዳደር ክላስተር ሰብሳቢና የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ እሸቴ አስፋው በበኩላቸው አገራዊ እድሎች እና ስኬቶችን ከፍ አድርጎ ለህዝባችን የማድረስ ፤ የማኅበራዊ ሚዲያ አርበኛ በመሆን አፍራሽ አስተሳሰቦችን መመከት ይገባል ብለዋል፡፡

ሙስናና ብልሹ አሰራርን የመከላከል እንዲሁም የብሄራዊ ገዥ ትርክትን በማስረጽ ሕብረ ብሄራዊነቷ የተጠበቀች አፍካሪዊት የብልፅግና ተምሳሌት አገር ለመገንባት አመራርና አባሉን በግንባር ቀደምነት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ የብልፅግና ወረዳ ፓለቲካ ዘርፍ ሃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ሃላፊ አቶ ሙሳ አሕመድ፣ የብልፅግና ወረዳ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ና የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የሐብት አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ አቶ ብርሀኑ ፈይሳ እንዲሁም የወረዳዉ አመራርና አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party