የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም የሚያስከብር የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስራዎችን በቅንጅት መስራት ይገባል
የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም የሚያስከብር የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስራዎችን በቅንጅት መስራት ይገባል
ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር)
በብልጽግና ፓርቲ ህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዘርፍ አስተባባሪነት ለፌዴራል ተቋማት የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስራዎችን በቅንጅት መስራት የሚያስችል የምክክር መድረክ በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ተካሂዷል።
የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስራዎችን በቅንጅት መስራት ባለፉት የለውጥ አመታት የተመዘገቡ ስኬቶችና ድሎችን በማጉላት የፓርቲ ቅቡልነትን ለማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል የብልጽግና ፓርቲ ህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር)
የብልፅግና ፓርቲ በፓለቲካ፣ በትርክት ግንባታ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶችን ማዝመዝገቡን አብራርተዋል።
በዚህም ፓርቲው በሀገረ መንግስትና ተቋም ግንባታ ላይ ጠንካራ አሻራ እያሳረፈ ይገኛል ብለዋል ዶክተር ቢቂላ።
የሚዲያና የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎችን አቅም በመገንባትና ቅንጅታዊ አሰራሮችን በመዘርጋት የፓርቲንና የመንግስትን ስኬቶችና ድሎች በወቅቱ ማስተዋወቅ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
አያይዘውም የዘርፉ ባለሙያዎች አሰባሳቢ ትርክቶች ላይ ያተኮሩ የሚዲያ ስራዎችን መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።
በቀጣይ በሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን በመቅረፍ በዘላቂነት የህዝብ ተጠቃሚነት በሚያረጋገጡና የሀገርን ገፅታ በሚቀይሩ የልማት ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።