ብልፅግና ፓርቲ ከሰራቸው ስራዎችና ካመጣቸው ለውጦች ይልቅ ገና ወገብ የሚያጎብጡ ዘመን ተሻጋሪ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ውጤት ለማምጣት ርብርብ እያደረገ የሚገኝ ህዝባዊ ፓርቲ ነው፡፡ ምክንያቱም ብልፅግና በዕውቀትና በዕውነት፣ለህዝብና ለሀገር የቆመ ግዙፍ ፓርቲ ነውና፡፡
ወጥ አቋም ያለው እና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት ለመገንባት ሌት ተቀን የሚጥረው ብልፅግና ትክክለኛና እውነተኛ ፌደራሊዝም በመተግበር ሀገሪቱን እንደ እሾህ ዙሪያዋን አጥረው ከያዟት ውስብስብ ሀገራዊ ፈተናዎች ለማውጣት በጠንካራ አመራሮቹና አባሎቹ አማካኝነት አበክሮ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ለውጥ እንዲሁ በምኞት የሚመጣ አይደለም፤ ዳገቱን መውጣት፣ ቁልቁለቱን መውረድ፣ለለውጥ ራስን በማዘጋጀት እጃችን እስኪሻክር ድረስ መልፋትና መጣር ይፈልጋል በጥቅሉ ፈተናዎችን መሻገር የግድ ይላል ማለት ነው፡፡
ብልፅግና ፓርቲ አንድ ትልቅ እምነት አለው፤እሱም ማንኛውንም ፈተናና ወጀብ ከህዝብ ጋር ማለፍ ወይም መሻገር ይቻላል ብሎ ያምናል፡፡ እንደ ሀገር የሚያጋጥሙንን ከባድ የሚመስሉ ነገር ግን በሁላችንም ንቁ ተሳትፎ ቀላል ማድረግ የምንችላቸው እንቅፋቶች አሉ፡፡
ለችግሮች በጋራ መፍትሔ እንሻለን እንጂ መቼውንም እጅ አንሰጥም፡፡ የዚህች ታላቅ አገር ሕዝብ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ፣ለህግ የበላይነት በሁሉም ቦታ መከበር፣ዜጎች የሰላም አየር መተንፈስ እንዲችሉ፣ለሚያጋጥሙ ሀገራዊ ችግሮች በጠረንጴዛ ዙሪያ የመፍትሔ ሀሳቦችን ማፍለቅና ለመሳሰሉት ሀገራዊ ጉዳዮች ለጋራ ብልፅግና በጋራ መነሳት ከቻልን የምንመኘውን የሀገራችን ኢትዮጵያ ብልፅግና በህዝባዊው የብልፅግና ፓርቲ ዕውን መሆኑ መቼም አይቀርም፡፡