You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

የክልል ሴክተር ብልጽግና ፓርቲ የመሰረታዊ ድርጅትና የህዋስ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት ጀመረ

የክልል ሴክተር ብልጽግና ፓርቲ የመሰረታዊና የህዋስ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ መስጠት ተጀመረ።

አቶ ካሚል ሀመድ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ እና የጽህፈትቤት ተወካይ ለሰልጣኞች የስልጠናውን መነሻ ሀሳብ ባቀረቡት ወቅት እንዳሉት አንድ ወጥ ሀገራዊ ብልጽግና ተመስርቶ የራሱ መተዳደሪያ ደንብ፣ መመሪያ እና አሰራር ስርዓት ተዘጋጅቶ በተግባር ላይ መዋሉን ገልጸው፤ በመመሪያዎቹ በተለይ አደረጃጀት መመሪያ፣ ዘመናዊ የአባላት መረጃ አያያዝ እና ወርሀዊ የአባላት መዋጮ አከፋፈል ላይ ለአመራሩ እና ለአባላቱ ግንዛቤ ለማሳደግ ስልጠናው ተዘጋጅቷል ብለዋል።

ስለ ብልጽግና ፓርቲ የአባላትና አመራር አካላት አደረጃጀት፣ ተልዕኮ እና አሰራር ሰነድ በአቶ ሀሰን አህመድ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ እየቀረበ ይገኛል።

ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ተከታይ ቀናት በሚሰጠው በዚህ ስልጠና ላይ የክልል ሴክተር ብልጽግና ፓርቲ የመሰረታዊ ድርጅትና የህዋስ አመራሮች ተገኝተዋል።

Leave a Reply