You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

/በሚራክል እውነቱ/ ምንጊዜም በለውጥ ሂደት ውስጥ አልፎ አልፎ በሚኖሩ ግርግሮች ውስጥ የሚታይ አቧራ አይጠፋም፤ይህ በየትኛውም ዓለም ላይ ያለና የሚኖር ሐቅ ነው፡፡ለዚህ ማስረጃ ይሆን ዘንድ አሜሪካን እንደ ምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡

ዓለም ላይ ካሉ እጅግ ከሰለጠኑና የዴሞክራሲ አባት ተብላ የምትጠራው ሀገረ አሜሪካ የፕሬዝደንት ትራምፕ የስልጣን ዘመን መጠናቀቁን አስመልክቶ በቅርቡ የተካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ዲሲን ጨምሮ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች አለመረጋጋቶች ስለመኖራቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ለውጥ በየቀኑ አይደለም በማይክሮ ሰከንድ ሊፈጠር ይችላል፡፡

ችግሩ ለውጡን መሸከም የማይችል ትክሻ ካለ ብቻ ነው፡፡በርግጥ ለውጥ ትዕግስት ይፈልጋል፡፡ለውጥ ከዕውቀትና ከእውነት ጋር ሆኖ ፣ጥበብ ከማስታወል ጋር ተዳምሮ ለውጥን ማምጣት ይችላሉ፡፡የሚመጡ ለውጦች ሁሉ ለህዝብ አዎንታዊ ናቸው ማለት ግን አይደለም፡፡

ለውጡን ባግባቡ መጠቀም ካልተቻለ ከመልካም ጎናቸው በተቃራኒ ሊሆኑ የሚችሉበት ዕድል ይኖራል፡፡ለዚህም ነው በሀገራችን አንዳንድ አካባቢዎች ከለውጡ ማግስት ጀምሮ አንዳንዱ በውሃ ቀጠነ ሌላው ደግሞ ምክንያት የለሽ ሰበቦች የተነሳ በሰዎች ላይ ጉዳት ከማድረስ ጀምሮ በህዝብና በመንግስት ንብረቶች ላይ ጉዳት ሲደርስባቸው የሚስተዋለው፡፡

በሚፈጠሩ ሁከትና ብጥብጦች መካከል የግል ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚሯሯጡ እንደማይጠፉ ዕሙን ነው፤ይህ አይነቱ አካሄድ ጊዚያዊ እንጂ ዘላቂ ሊሆን አይችልም፡፡በብልጽግና ዘመን የመጣውን ሀገራዊ ለውጥ ከዚህም በላይ በአግባቡ ለማጣጣም አስተዋይነትን ይፈልጋል፡፡

ሀገራችን በበርካታ ሀገራዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ተከባ ነው ያለችው፡፡ከከበባት ተግዳሮቶች ለማውጣት ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ልንቆም ያስፈልጋል፡፡ይህንን ማድረግ ደግሞ እንችላለን፤ምክንያቱም አንድነት የቆዬ ኢትዮጵያዊ መገለጫችን ነውና፡፡

በሀገር ውስጥም በህዝብ መካከል ሰላማዊ ግንኙነትና አንድነት እንዲጠናከር እና ኢትዮጵያ እንደ ብዝህነቷ ያካበተቻቸው የመቻቻልና አብሮ የመኖር ባህልና የአንድነት መንፈስ እንዳይሸረሸር እና ለለውጡ እንቅፋት ከሚሆኑ ነገሮች በመራቅ የጋራ ሰላማችንን ከመዳፋችን አጥብቀን ልንይዘውና ልንጠብቀው ይገባል፡፡

ለውጥ ሰላምን በጽኑ ይፈልጋል፡፡ሰላምን ማስጠበቅ ደግሞ ከእኔ፣ካንቺና ካንተ በጥቅሉ ከእያንዳንዱ ሰው ይጠበቃል፤ ሰላም የሚመነጨው ከእያንዳንዱ ቤትና ግለሰብ እንጂ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ብቻ ሊረጋገጥ አይችልምና ሰላማችን እንዳይደፈርስና የምንፈልጋትን የበለጸገች ኢትዮጵያ ዕውን ትሆን ዘንድ እንዲሁም ለውጡን በአግባቡ ለማጣጣም ሰላማችን በእጃችን መሆኑን ምንጊዜም ማስታወስ ተገቢ ነው፤ እያልኩ የገጠሙንን የጋራ ፈተናዎች በድል እንደምንሻገራቸው ከብልጽግና ጋር እምነቴ ነው፤ሰላም!

በህብር ወደ ብልጽግና !

ምላሽ ይስጡ