ፖለቲካ ፓርቲዎች በፖለቲካ ሥርዓት ግንባታዉ ዉስጥ አወንታዊ ሚና እንዲጫወቱ እየተደረገ ነው፡- አቶ ፓል ቶት
ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተቀራርበን መስራት በመቻላችን በፖለቲካ ሥርዓት ግንባታዉ ዉስጥ አወንታዊ ሚና እንዲጫወቱ እየጠደረገ ነው ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት ዘርፍ ምክትል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፓል ቶት ተናገሩ፡፡
በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ውስጥ እንደ መሪ ፓርቲ ትልቅ ሚና ይጠበቅብናል ያሉት አቶ ፓል ከፓርቲዎች ጋር ተቀራርበን መስራታችን እንደ አገር የሚኖረንን የብልጽግና ጉዞ ለማፋጠን ይረዳሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች የማህበረሰቡን ጉድለቶች እንዲሞሉና ለችግሮቻቸው አፋጣኝ መፍትሔዎችን እንዲያመቻቹ እንደ መሪ ፓርቲ አስፈላጊውን ድጋፍ ይደረጋልም ብለዋል፡፡
በፓርቲው የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲቪክ ማህበራት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ አባጊሳ በበኩላቸው ባለፉት ሶስት ወራት የአፍሪካዊያን የወንድማማችነት መድረክ እንዲፈጠር መደረጉ ለፓን አፍሪካኒዝም መጎልበት ትልቅ ዕድል የፈጠረ ነው ብለዋል፡፡
አህመድ አያይዘውም በክልሎች በኩል ያለው የአፈጻጸም ልዩነት መኖር፣በአንዳንድ ክልሎች በኩል ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ አለመስራት፣የሁኔታ ጥናት ሪፖርት አለመላክና መሰል ችግሮች የተነሱ ሲሆን በሁለተኛው ሩብ ዓመት ግምገማ እንዲህ አይነቱ የአፈጻጸም ችግር መስተካከል ይኖርበታል ብለዋል፡፡
በሁለቱም ሊጎች በኩል አገር ለማዳን በተሰሩ ስራዎች ላይ ያበረከቱት አስተዋጾኦ ይበል የሚያሰኝ እና በሌሎች ዘርፎችም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ባለፉት ሶስት ወራት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ትግበራ ምዕራፍ ድረስ ያከናወኗቸውን ተግባራት የሚመለከት ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በመጨረሻም ከተሳታፊ ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች በተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ በመስጠት የሩብ ዓመቱ የዘርፍ ግምገማ ተጠናቋል፡፡