You are currently viewing ለዜጎች ክብር የሚሰጠው ብልፅግና ፓርቲ

ለዜጎች ክብር የሚሰጠው ብልፅግና ፓርቲ

  • Post comments:0 Comments
ዜጎቿን ያላከበረች አገር በሌሎች ልትከበርና ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ ሊኖር አይችልም፤ ዜጎቿን በሁለንተናዊ መልኩ ማክበር የቻለች አገር ግን ለዜጎቿ በሰጠችው ክብር ልክ ከፍ ብላ ትታያለች፣ ሉዓላዊነቷም ተከብሮ ትኖራለች፡፡ አገር ዜጎቿን ትመስላለች የሚባለውም ለዚህ ነው፤ ዜጎችም የአገራቸው ገጽታዎች ናቸውና፡፡
ብልጽግና ፓርቲ በመደመር መስመር መዳረሻውን በሁለንተናዊ ብልጽግና ለማሳካት ጉዞ የጀመረው የዜጎችን ክብር በማስቀደም ነው፡፡ ብልጽግና የዜጎች ወይም ሰዎች ክብር በአገር፣ በቡድንና በግለሰብ ደረጃ የሚገለጽ መሆኑን በማመን እንዲሁም የአገር ክብር የግለሰቦች የወል ክብር መሆኑን በጥልቅ በመረዳት ኢትዮጵያዊያን የሚመኙትንና ሁልጊዜም እየፈለጉና እየሞከሩ በሚፈልጉት ልክ ያላገኙትን ሰው በመሆን የሚቀድም አብሮነት እውን ለማድረግ እየሰራ ያለ የህዝብ ፓርቲ ነው።
ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ለረጅም ዓመታት እየፈተናቸው ያለውን ጉድለትና ጉድለቱን ሞልቶ ወደ ብልፅግና ለማሸጋገርም ቀዳሚው ጉዳይ የዜጎች ክብርን ማረጋገጥ በመሆኑ ለዜጎች ክብር የትኛውንም አይነት ዋጋ በመክፈል ብልፅግናን ለማረጋገጥ ቆርጦ ተነስቷል።
በብልጽግና እምነት ሰዎች ወይም ዜጎች ሁልጊዜም ወደ ግብ መቅረቢያ መንገድ ሳይሆኑ ራሳቸው ግብ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ሰዎች አንድን ነገር ለማግኘት ወይም ለማሳካት ሲባል ብቻ የሚያስፈልጉ፣ አለያም ገሸሽ የሚደረጉ አይደሉምና፡፡ ይልቁንም ዜጎች በራሳቸው ከሁሉም ነገር ቀድመው የሚቀመጡ፤ የሚከበሩ፣ በማንነታቸውም ሳይሸማቀቁና ሳያፍሩ ቀና ብለው መሄድ የሚችሉ መሆናቸውን ማመን ይገባል፡፡
ብልጽግና ስለ ዜጎች ክብር መናገር ብቻ ሳይሆን፤ የተናገረውንና ያመነበትን እየተገበረ ያለ ፓርቲ ነው፡፡ በዜጎች መከበር ውስጥ የአገር ክብርና ሉዓላዊነት እውን እንደሚሆንም በጥልቅ ያምናል፡፡ እምነቱን እውን ለማድረግም ገና ከጥንስሱ በለውጥ ማግስት ያከናወናቸው ዜጋ ተኮር ተግባራትና በአገር ውስጥና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን በአደባባይ የገለፁት እምነትና ያሳዩት ተስፋ ህያው ምስክር ነው፡፡
በዛሬው ዕለት እንግልት ውስጥ የነበሩ ከሳውዲ የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ብቻ ሳይሆን ተመላሾችን በማደራጀትና መስራት የሚፈልጉትን በተለያዩ ዘርፎች በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በማደራጀት የራሳቸውን ስራ ፈጥረው እንዲሰሩ ለማድረግ በብልጽግና ፓርቲ በሚመራው መንግስት የተለያየ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

ምላሽ ይስጡ