መንግስት አካታች ብሔራዊ…

መንግስት አካታች ብሔራዊ…

  • Post comments:0 Comments
መንግስት አካታች ብሔራዊ የውይይት መድረክ ለመፍጠር እያሳለፋቸው ያሉት ውሳኔዎች ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት ያሳያል በሚል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝና የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር የሆኑት ሙሳ ፋቂ ምስክርነታቸውንና አድናቆታቸውን መግለጻቸው ይታወቃል።
በአንድ አገር ውስጥ አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ኖሮም አያውቅም፤ሊኖርም አይችልም። በሁሉም ነገር መግባባት ከቶም አይቻልም፤ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው የራሱ ምልከታና ግምት አለውና።
ሆኖም ግን ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን በማድረግ እንደ አገር ለድርድር በማይቀርቡ ወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መክረን ለአገር ቀጣይ ሰላም፣ልማትና ብልጽግና ደጀንነታችንን ልናሳይ ይገባል የሚል ምልከታ አለው ብልጽግና ፓርቲ።
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ “የፖለቲካ ሥርዓቱ የአሸናፊ ሳይሆን የመግባባት እንዲሆን አብረን እንሠራለን፤በንግግር እና በምክክር ለአንገብጋቢ ችግሮች መፍትሔ እናገኛለን፤አካታች ብሔራዊ የውይይት መድረክ እናካሂዳለን፤ችግሮቻችንን በጠረጴዛ ዙርያ የምንፈታበት ይሆናል” ማለታቸው የሚታወስ ነው።
ይህ አካታች የምክክር ሒደት ችግሮቻችንን በጠረጴዛ ዙሪያ ይፈታሉ ብለው የሚያምኑትን የሚያካትት፤ በፖለቲካ ልሒቃን መካከል ብቻ የሚደረግ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ያገናዘበ አጠቃላይ ሒደቱ አካታች እና አሳታፊ እንዲሁም በኢትዮጵያውያን እየተመራ ሀገር በቀል መፍትሔዎች ለማፍለቅ ታልሞ የሚከናወን ስለመሆኑ የብልጽግና ፓርቲም በተደጋጋሚ እየገለጸ ይገኛል።
ስለሆነም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ለዚህ አካታች ብሔራዊ የምክክር መድረክ ስኬታማነት የየበኩላችንን አስተዋጾኦ በመወጣት የታሪክ ተካፋይ ልንሆን ይገባል።

Leave a Reply