You are currently viewing “አፍሪካውያን ለኢትዮጵያ እውነተኛ ድጋፍ እያደረጉ ነው”፦ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

“አፍሪካውያን ለኢትዮጵያ እውነተኛ ድጋፍ እያደረጉ ነው”፦ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

  • Post comments:0 Comments
“አፍሪካውያን ለኢትዮጵያ እውነተኛ ድጋፍ እያደረጉ ነው”፦ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
 
በዓለም ዙሪያ ምዕራባውያንን ለመቃወምና ኢትዮጵያን ለመደገፍ እየተካሄዱ ባሉ የድጋፍ ሰልፎች አፍሪካውያን በተለይ ጎረቤት አገሮች ለኢትዮጵያ እውነተኛ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ።
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በተለይ ለኢ.ፕ.ድ እንዳስታወቁት፤ ሰሞኑን በተለያዩ የዓለም አገራት በተጠራው ሰልፍ ላይ በርካታ አፍሪካውያን በተለይ ጎረቤት አገሮች ለኢትዮጵያ እውነተኛ ድጋፋቸውን አሳይተዋል።
 
በውጭ አገር የነበረው እንቅስቃሴ እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ በማለት ከ27 በላይ በሚሆኑ የአውሮፓ ከተማዎች አፍሪካውያንን በተለይ ጎረቤት አገራት ኤርትራውያን፣ ኬንያውያንና የሶማሊያ ዜጎችና የኢትዮጵያን ወዳጆችን ጨምሮ በጋራ ወጥተው ኢትዮጵያን አትንኩ፤ እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ ሰብስቡ የሚል መልዕክት ማስተላለፋቸው የኢትዮጵያ ጉዳይ የአፍሪካ መሆኑን አመላካች ነው ሲሉ ገልጸዋል።
 
እንደ አምባሳደሩ ገለጻ፤ በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቻቸውና ዘመዶቻቸው የሚያነሱትን ጥያቄ በመረዳት የሕልውና ዘመቻውን መደገፋቸውን በጉልህ ታይቷል።

ምላሽ ይስጡ