ህዝብና መንግስት የአገርን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ከውጭ ጠላቶች እና የውስጥ የሽብር ቡድኖች ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ገብተዋል – ዶ/ር አብርሀም

ህዝብና መንግስት የአገርን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ከውጭ ጠላቶች እና የውስጥ የሽብር ቡድኖች ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ገብተዋል – ዶ/ር አብርሀም

  • Post comments:0 Comments
ህዝብና መንግስት የአገርን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ከውጭ ጠላቶች እና የውስጥ የሽብር ቡድኖች ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ገብተዋል – ዶ/ር አብርሀም
ህዝብ እና መንግስት አገራችን ኢትዮጵያ ላይ የተከፈቱትን ዘርፈ ብዙ የውጊያ አውዶች በሚገባ አጥርተው ለይተው ራስን የመከላከልና የአገራችንን ሉአላዊነትና ግዛታዊ አንድነት ለማስጠበቅና ለማስከበር ከውጭ ጠላቶች እና የውስጥ የሽብር ቡድኖችና ባንዳዎች ጋር ግልፅ ትንቅንቅ ውስጥ ገብተዋል ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሀም በላይ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ይህንን የተናበበና የመጨረሻ ግቡ የተዳከመችና ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ የማትችል ደካማ አገር የማረጋገጥ ፍላጎት፣ የተበተነና በግዛትም ጭምር የተከፋፈለ ህዝብና አገር የማስፈን ቅዠት፣ የቀጠናውን አለመረጋጋትና አለመተማመን በመጠቀም ለአመታት የሚዘልቅ ኢፍትሐዊ የብሔራዊ ጥቅሞችን የማቋቋምና የማደላደል ሴራ ስሪት ግልፅ እሽቅድምድም ነው ብለዋል።
ከዚህ ባለፈም በታላቅ ህዝባዊ ይሁንታ ከመጣው የኢፌዴሪ መንግስትና በታሪኩ፣ በማንነቱ፣ በጀግንነትና በፅኑ ተምሳሌታዊ ገድሎቹ ደምቆ በነቂስ በከተተውና በደጀንነት በተሰለፈው የኢትዮጵያ ህዝብ ፊት ፀሐይ የሞቀው ገሐድ ጉዳይ ነው ሲሉም ገሀልጸዋል።
መከላከያ ሰራዊታችን፣ የሚሊሻ፣ ልዩ ሐይልና አጋዥ ህዝባዊ የፀጥታ አደረጃጀቶቻችን በአገር ውስጥና በውጪ ካለው ደጀን ህዝባችን ጋር በመቀናጀት ለክተቱ እየሰጡ ያለው ፈጣን ምላሽ አኩሪ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ይህንን በውጊያ፣ በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንዲሁም በሚዲያና የስነ-ልቦና ጫና ጭምር የሚገለፅ ጦርነትና በሁሉም አቅጣጫ የሚዘንበውን ጥቃት መንግስትና ህዝባችን በተገቢው በመመከት የአባቶቹን የነፃነት ተጋድሎ ታሪክ ለመድገም በአንድ ተሰልፏልም ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።
ባንዳው የሽብር ቡድኑ ሕወሓት የጥፋት ጀሌዎቹና ሸኔ ከውስጥ፣ በታሪካዊ ጠላትነታቸው የፀኑና ጥቅም መር ፍላጎታቸውን በጉልበት ለመጫን የሚታትሩ ግልፅ የውጭ ጣልቃ ገብ ሐይሎች ከደጅ፣ መንግስትና ህዝባችን አምርረው የሚታገሏቸው ጠላቶቻችን ናቸው ብለዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

Leave a Reply