You are currently viewing በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች የሽኝት መርሀ ግብር ተደረገ

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች የሽኝት መርሀ ግብር ተደረገ

  • Post comments:0 Comments
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች የሽኝት መርሀ ግብር ተደረገ።
በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ የሲዳሞ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የት/ት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሳ ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ፣የሀዋሳ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች፣የሃይማኖት አባቶች እና በዛሬው ዕለት መከላከያ ሰራዊታችንን ለመቀላቀል በፍቃደኝነት የተመዘገቡ ወጣቶች በተገኙበት ተከናውኗል ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሽኝቱ ፕሮግራም ላይ በመገኘት ባስተላለፋት መልእክት እንደተናገሩት ሲዳማ ዛሬ ጀግኖች ልጆቹን እየላክ እንደሚገኝ በማንሳት ለዘመናት ኢትዮጵያውያን ጫንቃ ላይ በመሆን ሀገሪቷን ሲበዘብዝ የቆየው ጁንታው ኃይል ኢትዮጵያን ለመበተን በማቀድ የውክልና ጦርነት እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረው ይህን ኃይል ለመመከት በዛሬው ዕለት ከመላው የሲዳማ ክልል በፍቃደኝነት ተመዝግበው ጀግናውን የሀገር መከላከያ ሰራዊታችንን ለመቀላቀል የወሰኑ ወጣቶችን በማመስገን በሄዱበት ሁሉ ድል እንዲቀናቹው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ።
በሽኝት መርሐ ግብሩም ላይ ከ10 መኪና በላይ ስንቅ ፣ከ200 በላይ የእርድ ሰንጋ በሬዎች ፣ከ400 በላይ በግ እና ፍየል ሙክቶች እንዲሁም በካሽ ከአመራሩ እና ከባለሀብቶች የተሰበሰበውን ብር 30 ሚሊዮን ብር ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፍ ተደርጓል።
በሽኝቱ ማብቂያም ላይ ሀገር ሽማግሌዎች ወጣቶቹን በሄዱበት ሁሉ ድል እንዲገጥማቸው በመመረቅ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና ካቢኔያቸው ጋር በመሆን የባንድራ ርክክብ አከናውነዋል።
የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት

ምላሽ ይስጡ