የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ የጸጥታና የልማት ጉዳይ ላይ እየተወያዩ መሆናቸው ተገለፀ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ የጸጥታና የልማት ጉዳይ ላይ እየተወያዩ መሆናቸው ተገለፀ

  • Post comments:0 Comments
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ የጸጥታና የልማት ጉዳይ ላይ እየተወያዩ መሆናቸው ተገለፀ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ የጸጥታና የልማት ጉዳይ ላይ እየተወያዩ መሆናቸው ተገልጿል።
አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ የውይይት መክፈቻ ባደረጉበት ወቅት አሸባሪ ህወሓት ቡድን በተደጋጋሚ በመንግሥት የተሰጠውን እድል ወደጎን በመተው ጦርነት ብቸኛ ምርጫ ማድረጉ ተገቢነት የለውም።
አቶ አስሃቅ አክለው የህዳሴ ግድብ የጸጥታው ምክር ቤት አጀንዳ ያደረጉት የውስጥ ባንዳዎችና የውጭ ጣልቃ ገብነት መሆኑን ገልጸው፤ ጉዳዩ በትግል ስርዓት እንዲይዝ ተደርጓል ብለዋል።
ሀገርን ከመበተን ለሚታደግ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ለክልሉ ጸጥታ ኃይል የሚደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል ጽ/ቤት ኃላፊው።
ክልሉን ሁለተኛ የትርምስ ቀጠና ለማድረግ የሚሯሯጡ ኃይሎችን ማህበረሰባችን ታግሎ እኩይ ተግባራቸውን ከማስቀረት ረገድ የዜግነት ግዴታውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ አቶ ኢስሃቅ ተናግረዋል።
በህዝብ ግንኙነት ስራዎችን የሀገርን ጉዳይ፤ የሀገር አንድነት በማስቀደም መስራት ይገባናል ብለዋል አቶ ኢሰሃቅ።

Leave a Reply