የዕዙ የሠራዊት አባላት አሸባሪውን የህውሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ግብዓተ መሬት ለማስገባት በአስተማማኝ የዝግጁነት ቁመና ላይ ይገኛሉ -ሜ/ጀ መሰለ መሠረት

የዕዙ የሠራዊት አባላት አሸባሪውን የህውሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ግብዓተ መሬት ለማስገባት በአስተማማኝ የዝግጁነት ቁመና ላይ ይገኛሉ -ሜ/ጀ መሰለ መሠረት

  • Post comments:0 Comments
የዕዙ የሠራዊት አባላት አሸባሪውን የህውሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ግብዓተ መሬት ለማስገባት በአስተማማኝ የዝግጁነት ቁመና ላይ ይገኛሉ -ሜ/ጀ መሰለ መሠረት
 
የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል መሰለ መሠረት የዕዙ የሠራዊት አባላት አሸባሪውን የህውሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ግብዓተ መሬት ለማስገባት በአስተማማኝ የዝግጁነት ቁመና ላይ እንደሚገኙ ተናገሩ፡፡
 
ሜጀር ጀነራል መሰለ ወደ ምዕራብ ዕዝ የተቀላቀሉትን መሰረታዊ ወታደሮች አቀባበል በተደረገላቸው ጊዜ እንደተናገሩት÷ እንደ እባብ አፈር ልሶ የተነሳው አሸባሪው የህውሓት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈርረስ ቢዳክርም የህልም ቅዠት ይሆንበታል፡፡
 
የዕዙ የሠራዊት አባላት ህግ በማስከበርና የህልውና ዘመቻ ወቅት የአሸባሪውን የህውሓት ቡድን አከርካሪውን በመስበርና የቡድኑን ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስራ በማዋል ለህግ እንዲቀርቡ በማድረግ የአንበሳውን ድርሻ የተወጣ ዕዝ ነው ብለዋል፡፡
 
ዕዙን ከተቀላቀሉ የሠራዊት አባላት በበኩላቸው የኢትዮጵያ ጠላት የሆነው አሸባሪው የህውሓት ቡድንን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Leave a Reply