የለውጥ ችቦ ተለኩሶ በሚያጓጓ የለውጥ ምህዋር ውስጥ አገራችን ከመግባቷ በፊት ይታዩ የነበሩ ሁሉን አቀፍ ችግሮች ህዝባችንን ተስፋ እንዲቆርጥ የሚገፋፉ እንደነበሩ ግልጽ ነው፡፡ የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሲጣሱ፤ ኢፍትሃዊነት ነግሶ በአንድ አገር ውስጥ አንዱ ቤተኛ ሌላው ባይተዋር ሆኖ የዜጎች እኩል የመጠቀም መብት በግልጽ ሲጣስ ጥቂቶች የህዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ የራሳቸውን ኪስ በማደለብ ተጠምደው ቆይተዋል፡፡
ብልጽግና በህዝብ ውስጥ የእኩልነት፣ የፍትሃዊነት እና የዴሞክራሲና መሰል ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ ከፍተኛ ፍላጎት በነበረበት ሰዓት ለአገራችን ህዝቦች የጨለመውን ድባብ ወደብርሃን ለመለወጥ የተፈጠረ ያለ ድርጅት ነው፡፡ብልጽግና አገራችን በእዳ ተዘፍቃ፤ ኢኮኖሚዋም ተንኮታኩቶ፣ ጥቂቶች የነገሱበት ብዙሃኑ ግን የበይ ተመልካች የሆነበትን የጨለማ ጊዜ ከመሰረቱ ለመቀየር በርካታ የለውጥ ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ የተስፋ ብርሃነ የሚታይባት አገር እንድትሆን ማድረግ የቻለ ፓርቲ ነው፡፡
ብልጽግና ፓርቲ የለውጥ አመራሩን በማቀናጀት እና የወንድማማችነት እሴት እንዲጎለብት በማድረግ ያስመዘገባቸው ሀገራዊ ቱርፋቶችን ስንመለከት ዕድሜ ለሰጠው ገና አጓጊና ተዓምራዊ ለውጦችን ማየቱ አይቀሬ እንደሆነ ከወዲሁ መገንዘብ ይቻላል፡፡
በመንገዳገድ ላይ የነበረውን የሀገራችንን ኢኮኖሚ ፈር ከማስያዝ ጀምሮ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ሪፎርም በማድረግ ለህዝቡ እንዲመቹ ሆነው በማዋቀር በአጭር ጊዜ የሚታይና የሚጨበጥ ለውጥ በሁሉም መስኮች ማስመዝገብ ጀምሯል-ብልጽግና፡፡
በሀገራችን እየጎመራና እየፈካ የሄደው አገራዊ ለውጥ ለዓመታት በህዝቡ ዘንድ ሲነሱ የቆዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታው እንዲጎለብት በቁርጠኝነት እየሰራ ያለው ብልጽግና ዛሬም ነገም ወደፊትም መዳረሻውን ለማሳካት የሚያስችለው ሁለንተናዊ ጥንካሬን የተላበስ አገራዊ ፓርቲ ነው፡፡
በመንግስታችንና በኢትዮጵያዊያን የጋራ ርብርብ የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል የተሠሩና መደገም የማይገባቸውን ስህተቶችን በማረም እንዲሁም ሊያግባቡን በሚችሉ የጋራ ጉዳዮቻችን ላይ በማተኮር ለመጪዉ ትዉልድ ጥቅም የሚተጋ ፓርቲ በመሆኑም ነው ብልጽግናን መምረጥ አገርን ወደፊት ማሻገር ነው የምለው፡፡
የህዝቦች የልማት፤ የዴሞክራሲ፤ የነፃነትና የእኩልነት ፍላጎት በዘላቂነት የተሟላበት ሀገር ለመፍጠር ብሎም በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ ሕብረ ብሄራዊ አንድነታችንን ለማጎለበትና እያጣጣምነው ያለው ሁለንተናዊ የልማት ቱርፋቶችን በዘላቂነት ለማስቀጠል ቁርጠኛ የሆነው ብልጽግና የሚበራ አምፖልን የመወዳደሪያ ምልክቱ አድረጎ ሲቀርብ መሰረታዊ መነሻው ጨለማ በብርሃን ፊት የመቆም ኃይል እንደሌለው ሁሉ፤ ጥላቻም በፍቅር ፊት፤ ቂምም በይቅርባይነት ፊት፣ ስግብግብነትም በጋር መስራትና በጋር ማደግ ውስጥ ጉልበት እንደሌላቸው ስለሚያምን ነው፡፡ በመሆኑም የብርሃን፤ የተስፋ ተምሳሌት የሆነውን አምፖልን በመምረጥ የሀገራችንን የመኖር ህልውና ልናስቀጥል ይገባል፤ምክንያቱም በብርሃን ፊት ደፍሮ የሚቆም ጨለማ የለምና፡፡
የወጣቶችንና የሴቶችን የስራ አጥነት ችግር በመቅረፍ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ባለፉት አመታት በመላ አገሪቱ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ወጣቶችና ሴቶች በተለያዩ ዘርፎች ተደራጅተው እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ ራሳቸውን እንዲለውጡ በለውጡ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጦት የሚገኝ አጀንዳ ነው፡፡ምክንያቱም ሀገራችን በወጣቶችና በሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ የምትገነባና እየተገነባች ያለች ሀገር ናትና፡፡ ይህም ሆኖ በአገሪቱ ከሚስተዋለው የስራ አጥነት ችግር ስፋትና መጠን ጋር ሲነጻጸር ግን በዚህ ረገድ የተሰሩ ስራዎች ገና በጅምር ደረጃ የሚታዩና ብዙ የሚቀራቸው እንደሆኑ ገዢው ፓርቲ ብልጽግና ያምናል፡፡
ብልጽግና በመላ አገሪቱ የሚስተዋለውን የስራ አጥነት ችግር ለመፍታት እያደረገ ያለውን ይህን መሰል ጥረት ውጤታማ ለማድረግ ከጉዳዩ ባለቤት ወጣቱ፣ ከሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ከአጠቃላይ ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል፡፡
ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው አድጎ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች እንዲተርፉ ብልጽግና አበክሮ እየሰራ ይገኛል ምክንያቱም በብርሃን ዘመን ማንም በጨለማ እንዲኖር አይፈቀድለትም ፤በለውጥ ዘመን ማንም ወደ ኋላ እንዲቀር ፓርቲው አይሻም፡፡በትናንትናው ዕለት ማለትም የካቲት 23 በመላ ሀገሪቱ ያከበርነው የአድዋ ድል በዓል ለአሁኑ ትውልድ የሚሰጠው ትምህርት በእጅጉ የበዛ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
ከኢትዮጵያውያን አልፎ ለመላው ጥቁር ህዝቦች መነቃቃትን የፈጠረው የአድዋ ድል በኢትዮጵያ ብዝሃነት ውስጥ ያለውን ጠንካራ አንድነት ጉልህ ፋይዳ ማሣያ ነው፡፡የአድዋ ድል አገራችንን የፀረ ቅኝ ግዛትና የጥቁር ህዝቦች ድልና ተምሳሌት እንዳደረጋት ሁሉ ወጣቱ ትውልድ በአገሪቱ የተጀመረውን የጸረ ድህነት ትግል ይበልጥ በማቀጣጠልም የአድዋን ድል በድጋሚ ሊያስመዘግብ ይገባዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡
በህብር ወደ ብልጽግና !