You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

ከወትሮው አዳዲስ ባህርያትን የተላበሰው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በምርጫ ቦርድም ይሁን በመንግሥት ዘንድ ከቀደምት አምስት ምርጫዎች በተለያዩ መንገዶች ተዓማኒና ፍትሐዊ እንዲሆን በቁርጠኝነት እየተሰራ እንዳለ ይታወቃል፡፡

ከኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መፍረስና ከብልፅግና ፓርቲ መመሥረት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረገው ይህ አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ያለ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ተሳትፎ የሚከናወን እና ነፍጥ አንግበው ሲንቀሳቀሱ የነበሩና ኑሯቸውን በውጭ አድርገው የነበሩ ነገር ግን በተፈጠረው ሀገራዊ ለውጥና የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት ጋር ተያይዞ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ በርካታ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚወዳደሩበት የምርጫ ዘመን እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ከምርጫው ጋር ተያይዞ የሚነሳውና በአንዳንድ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዘንድም ትኩረት ሊሰጠው ይገባል በሚል የሚነሳው ጉዳይ አገራዊ የፀጥታው ሁኔታ ሲሆን በተለያዩ አካባቢዎች አልፎ አልፎ ብልጭ እያለ ያለውን የፀጥታ ጉዳይ ፈር ማስያዝ ከሁሉም አካላት የሚጠበቅ ስራ ነው፡፡

ሆኖም ግን አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚኖር የጸጥታ ችግር እንደ ሀገር ለምናካሂደው ምርጫ እንቅፋት ሊሆን አይችልም፡፡ምክንያቱም ሁሌም ቢሆን የተመቻቸ ሁኔታ ይፈጠራል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ስለሚሆን የሚገጥሙንን ፈተናዎች በድል እየተሻገርን ለውጤት መብቃት የግድ ይላል፡፡

ምላሽ ይስጡ