You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

በብልጽግና ዘመን የመጣውን ሀገራዊ ለውጥ ከዚህም በላይ በአግባቡ ለማጣጣም አስተዋይነትን ይፈልጋል፡፡ ሀገራችን በበርካታ ሀገራዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ተከባ ነው ያለችው፡፡ከከበባት ተግዳሮቶች ለማውጣት ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ልንቆም ያስፈልጋል፡፡ይህንን ማድረግ ደግሞ እንችላለን፤ምክንያቱም አንድነት የቆዬ ኢትዮጵያዊ መገለጫችን ነውና፡፡

በሀገር ውስጥም በህዝብ መካከል ሰላማዊ ግንኙነትና አንድነት እንዲጠናከር እና ኢትዮጵያ እንደ ብዝሃነቷ ያካበተቻቸው የመቻቻልና አብሮ የመኖር ባህልና የአንድነት መንፈስ እንዳይሸረሸር እና ለለውጡ እንቅፋት ከሚሆኑ ነገሮች በመራቅ የጋራ ሰላማችንን ከመዳፋችን አጥብቀን ልንይዘውና ልንጠብቀው ይገባል፡፡

ለውጥ ሁሉም ይፈልጋል፡፡የቆዬ አብሮነታችን እንዳይደፈርስና የምንፈልጋትን የበለጸገች ኢትዮጵያ ዕውን ትሆን ዘንድ እንዲሁም ለውጡን በአግባቡ ለማጣጣም ሰላማችን በእጃችን መሆኑን ምንጊዜም ማስታወስ ተገቢ ነው፤የገጠሙንን የጋራ ፈተናዎች በድል ለመሻገርና ሀገራችን በብልጽግና ማማ ላይ ሆና ለማዬት የእርስ በእርስ መደማመጥ መሰረት መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡

Leave a Reply