አበው ሲመርቁ “እራትና መብራት አይንሳችሁ” ይላሉ፡፡ ለእንቅልፍ እራትም ሆነ ማታ ለጨለማው መብራት መፍትሄ እንደሚሆን ለመንገር ሲፈልጉ ፡፡ ምግብ መሰረታዊ እንደሆነ ሁሉ ብርሃንም ለሰው ልጆች በሙሉ አስፈላጊ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡
ብልጽግና በድህነት ጥግ ላይ የምትገኝን ሀገር ታሪኳን በመቀየር ህዝቦቿ በፍትሃዊነት የልማት ተጠቃሚዎች ለማድረግ አልሞ እየሰራ ነው፡፡ጨለማን የሚሻ የለም፡፡ ሁሉም ብርሃንን ፍለጋ ይጓዛል፡፡እርግጥ ነው በዘመነ ብልጽግና ጨለማ ቦታ አይኖረውም፡፡
ጨለምተኝነት፣ጸረ ዴሞክራሲያዊነት፣ከፋፋይነት፣ጸረ-ኢትዮጵያዊነት እና የአፈና ጊዜ አልፏል፡፡ጊዜው የብርሃን ነው፡፡ዴሞክራሲ ያበበበት፣ኢትዮጵያዊ አንድነታችን የጎለበተበት፣ህብረ ብሔራዊነታችን ያጠናከርንበት፣ከድህነት አዙሪት ለመውጣት የምንታትርበት እና በምናገኘው የልማት ቱርፋት እኩል ተጠቃሚ ለመሆን የምንሰራበት፣መተሳሰባችን የበለጠ ከፍ ያለበት በብልጽግና ዘመን ነው፡፡
ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚሹ ከውስጥና ከውጭ ሀይሎች ጋር በአስተሳሰብም ሆነ በተግባር ገጥመን ውጤት ያመጣንበት ፣አንድነታችንን ለመሸርሸር ከሚፈልጉ ቡድኖች ጋር እልህ አስጨራሽ ትግል በማድረግ መተሳሰባችንን ያጎለበትንበት፣ዝቅ ይላሉ ሲሉ ከፍ ያልንበት፣በዘርና በሐይማኖት ተከፋፍለው እርስ በእርስ ግጭት ይፈጥራሉ ሲሉን ተቻችለን መኖር የጀመርነበት በብልጽግና ዘመን ነው፡፡
በርግጥ ብርሃንን የሚጠሉ ይኖራሉ፡፡እነሱም ሌቦች ብቻ ናቸው፡፡የህዝብንና መንግስትን ሀብትና ንብረት ለመዝረፍ የሚመቻቸው ማንም ሰው በማይኖርበት ወይም በማይንቀሳቀስበት ጨለማ በሆነ ጊዜ ነው፡፡ለዚህ ነው ብርሃንን ያዩ ሁሉ ይደነግጣሉ፤አይመቻቸውም፡፡ ዕድሜ ለብልጽግና ጨለማን ተገን አድርገው ህዝባችንን ከሚያውኩና ከሚሰርቁ ሀይሎችና ቡድኖች ሊታደገን ብርሃንን መርጧል፡፡