You are currently viewing ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ብልጽግና ፓርቲና መንግስት በቀጣይ ስራዎቻቸውን የበለጠ እንዲሰሩ ያነሳሳ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ብልጽግና ፓርቲና መንግስት በቀጣይ ስራዎቻቸውን የበለጠ እንዲሰሩ ያነሳሳ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

  • Post comments:0 Comments

በኦሮሚያ ክልል ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ብልጽግና ፓርቲና መንግስት በቀጣይ ስራዎቻቸውን የበለጠ እንዲሰሩ ያነሳሳ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡ርዕሰ መስተዳድሩ በኦሮሚያ ክልል ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ለብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ ለወጡ የክልሉ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ከሁሉም በላይ ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነት በሰላማዊ መንገድ ይህን ሰልፍ አዘጋጅቶ እስከመጨረሻው ያለምንም ችግር በመጠናቀቁ የላቀ ምስጋና አለኝ ብለዋል፡፡በተለይም የፀጥታ አካላትና ወጣቶች እንዲሁም የሚዲያ አካላት ሰልፉ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በክልሉ ትናንትና ዛሬ በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች የተደረጉ የድጋፍ ሰልፎች ያለምን ችግር መጠናቀቃቸው አራት ትልቅ መልዕክቶችን ያስተላለፉ ናቸው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡በዚህም የክልሉ ህዝብ ጥቅሙን እና መብቱን በደንብ የተረዳ መሆኑን፣ ሰልፉ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የብልጽግና አመራር እስካሁን ያስመዘገቡትን ድል ለማመስገን፣ ለመደገፍና በቀጣይ ለሚያከናውኑት ስራ ህዝቡ ያለውን ድጋፍ ያሳየበት መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም ሰልፉ ጁንታው በመከላከያ ሰራዊት ላይ በፈጸመው ጥቃት ህዝቡ ቁጭቱን የገለጸበት መሆኑን ያሳየ እንደነበርም አስረድተዋል፡፡የታየው የህዝቡ ሞራልና መነሳሳት ብልጽግና ፓርቲና መንግስት በቀጣይ ስራዎቻቸውን የበለጠ እንዲሰሩ ያነሳሳ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ምላሽ ይስጡ