You are currently viewing የብርሃን ዘመን ያድርግልን! አሜን በሉ ! /በሚራክል እውነቱ/

የብርሃን ዘመን ያድርግልን! አሜን በሉ ! /በሚራክል እውነቱ/

  • Post comments:0 Comments

ምርጫ 2013 ትክክለኛና እውነተኛ ምርጫ የሚካሄድበት፣ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ቅድሚያ በመስጠት ለህዝብ ሰላም ዘብ የምንቆምበት፣ምርጫው ሐቀኛና ተዓማኒና የዳበረ ዴሞክራሲ የሚሆንበት፣በሕዝብ ውስጥ የሚብላሉ ማናቸውም ዓይነት ጥያቄዎች ለመፍታት የምንዘጋጅበት፣ አስተያየቶችና ጥቆማዎች በጥቅሉ ብሶቶች ለማስወገድ የምንፎካከርበት ታሪካዊ ምርጫ ይሁንልን፡፡

ከህዝብ ሰላም ይልቅ ስልጣንን አስቀድመን ግርግርና ሁከት ተፈጥሮ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ከመድረሱ በፊት በአገሪቱ ውስጥ እየነፈሰ ያለው ብሔር ተኮር አየርና ፖለቲካዊ ትግሉ ማስታዋል ወደ ታከለበት ብሎም እንደ ሰለጠነ ዜጋ በውይይት አምነን በሰላማዊ ሁኔታ ችግሮችን ለመፍታትና ምርጫውን አሸንፈን ስልጣን ለመያዝ ያብቃን እላለሁ፡፡

ለዚህም በመጀመሪያ ሁሉም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉ ቅድሚያ ለሀገርና ለህዝብ በማሰብ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ተፎካካሪነት መንፈስ የመለወጥ እሳቤን ሊያዳብሩ ይገባል፡፡ ይህም ጊዜው የሚጠይቀውን ሀገራዊ አስተሳሰብና መልካም ስነ ምግባር ይዞ መገኘት ቅድሚያ የሚሰጠው ቦታ ነውና ይህን ለማድረግ የሚያስችል ልቦና ይስጠን፡፡

ጥያቄን የማንሳት መብት ጨዋነት በተሞላበት መንገድ እርስ በእርስ በመናበብ የሚፈታበት ፣ በፖለቲካዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች በጥቅሉ በሕዝብ ጥያቄዎች ላይ በጠረንጴዛ ዙሪያ እየተደማመጡና እየተነጋገሩ፣ የሀሳብ ልዩነትነቶች እያከበሩና ለችግሮቹ የጋራ መፍትሔ እያስቀመጡ ጠንካራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ብሎም ሀገራዊ ለውጡ ቀጥሎ አገራዊ መግባባት የሚፈጠርበት የምርጫ ምዕራፍ ያድርግልን ፡፡

ቅድመ ምርጫም ይሁን ድህረ ምርጫው ብሩህ ተስፋ የምንሰንቅበት፣ ለፀብና ለግጭት መንስዔ ከሆኑ አጓጉል ድርጊቶች ራሳችንን የምናርቅበት ፣ ከደቦ ፍርድ እና በኃይል ለማስፈፀም ትግል ከማድረግ ይልቅ ችግሮቹ ወይም ጥያቄዎቹ በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበትን ሁኔታ የምናመቻችበት፣ የወጣቶችና የሴቶች፣የምሁራን፣የመንግስት ሰራተኞች በአጠቃላይ የህዝቡን ጥያቄዎች ከልብ በአንክሮ አዳምጦ በፍጥነት ምላሽ የሚያገኙበት፣ የአገርንና የሕዝብን ሰላም የሚያናጉ፣ ለዕልቂትና ለውድመት የሚያጋልጡ ጥላቻዎች፣የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ተወግደው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ጎልብቶ የሚያግባቡን መፍትሔዎች የሚመነጩበት፣ በማንነትና በብሔር ጥላቻ ላይ የተመሠረቱ አውዳሚ ሐሳቦች በኢትዮጵያዊነት ጠንካራ የአንድነት ስሜት በፍቅር የሚረቱበት እንዲሆን ሁሉም የምርጫ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስበው የሚሰሩበት ያድርግልን፡፡

በህብር ወደ ብልጽግና !

ምላሽ ይስጡ