You are currently viewing የህወሀት የጥፋት ቡድን ላይመለስ ተደምስሷል-ዶ/ር ቀንዓ ያደታ

የህወሀት የጥፋት ቡድን ላይመለስ ተደምስሷል-ዶ/ር ቀንዓ ያደታ

  • Post comments:0 Comments

የህወሀት የጥፋት ቡድን ላይመለስ ተደምስሷል ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ገለጹ።የመከላከያ ሚኒስትሩ በህወሀት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው በህግ ማስከበርና ህልውና ዘመቻው ወቅት ዕጅ ሰጥተው በደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል የተሃድሶ ስልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙትን የትግራይ ክልል ልዩ ሃይል እና የሚሊሻ አባላትን ባወያዩበት ወቅት ነው ይህን ያሉት።

የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር ቀነዓ ያደታ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፣”ደም መጣጩ ቡድን እናንተን እሳት ውስጥ ማግዶ ተደምስሷል” ብለዋል፡፡ትህነግ ለግል ጥቅሙ እና ለስልጣን ጥማቱ ሲል እኩይ ተግባራትን በኢትዮጵያውያን ላይ ፈጽሞ ላይመለስ ተወግዷል፡፡”እናንተ ግን በውሸት ወሬ ሳትረበሹ ስልጠናችሁን በማጠናቀቅ ወደ ሰላማዊ ህይወታችሁ መመለስ አለባችሁ” ብለዋል፡፡

የህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌ/ጀ ሀሰን ኢብራሂም በበኩላቸው ፣ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከጁንታው ጋር የተሰለፉ ዜጎችን ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

እጅ የሰጡት አባላት በበኩላቸው ፣”ግዴታ ሆኖብን ብንሰለፍም ምንም ሳንተኩስ እጃችንን ከሰጠንበት ጊዜ አንስቶ የመከላከያ ሰራዊታችን እያደረገ ላለው እንክብካቤ ምስጋና እናቀርባለን” ብለዋል፡፡በቀጣይ ለሃገራቸው ሰላም በጋራ እንደሚቆሙም አረጋግጠዋል፡፡

በደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል 764 ዜጎች የተሃድሶ ስልጠና እየወሰዱ ነው ተብሏል::የመከላከያ ሚኒስትሩ አባላቱን ባወያዩበት መድረክ ላይ ሌ/ጀ ሀሰን ኢብራሂምን ጨምሮ ሌሎች ጀነራል መኮንኖች እና የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ ነቢዩ ስሁል ተገኝተዋል፡፡

ምላሽ ይስጡ