You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

ግድቡ ኢትዮጵያ ያላትን አካባቢያዊም ሆነ አህጉራዊ አቅም እንደሚያጠናክርና ብሔራዊ ክብሯን እንደሚያስጠብቅ የአደባባይ ሐቅ ነው፡፡ግድቡ ለዜጎች ብሔራዊ ኩራት ከመሆኑም ባሻገር በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያና ፖለቲካዊ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ለህዝቡ የሚሰጠው ጠቀሜታ በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እኛ ኢትዮጵያዊያን ከድህነት ለመውጣት የምናደርገውን ጥረት እውን ማድረጊያ እንደ ዓይን ብሌናችን የምንመለከተው የጋራ ፕሮጀክታችን ነው፡፡ ብልጽግና በመጨረስ እንጂ በመጀመር አያምንም፡፡

ብልጽግና በስራ እንጂ ብዙ በማውራት አይገኝም፡፡ለዚህም ነው ማመን የሚከብዱ ድንቅ ስራዎችን መስራት የተቻለው፡፡ በርካታ ቢሊዬን ብር ወጪ ሆኖባቸው ከተጓተቱ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል ታላቁ የህዳሴ ግድብ አንዱ ነው፡፡

ይህ ፕሮጀክት በታቀደለት ጊዜ ተጠናቆ ቢሆን ኖሮ ለሀገር የሚያበረክተው አስተዋጾኦ ከፍተኛ ነበር፡፡ በማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ዘርፈ ብዙ ምላሾችን ማግኘት ይቻል ነበር፡፡የሆነው ሆኖ ብልጽግና ፓርቲ እንደ ፓርቲ የህዝብ ንቅናቄዎችን በመፍጠር ታላቁን ህዳሴ ግድብ በማጠናቀቅ እና የተጀማመሩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በመጨረስ ለህዝብና ለሀገር ጥቅም ላይ እንዲውሉ የርብርብ ማዕከል አድርጎት በትኩረት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ምላሽ ይስጡ