You are currently viewing የቦንጋ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎችን አስመረቀ

የቦንጋ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎችን አስመረቀ

  • Post comments:0 Comments

የቦንጋ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን 827 የበኩር ተማሪዎቹን አስመርቋል፡፡ክቡር አቶ ብናልፍ ለተማሪዎቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትና ንግግር ያደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያ የጀመረችው የብልጽግና ጉዞ እንዲሳካ “ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲው ቆይታ ያካበቱትን ወንድማማችነት፣ ሠላም፣ መከባበርና መዋደድ ልምዳቸውን አጠናክሮ እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።”ወጣቱ ትውልድ ያለፉ ስህተቶችን በማረም፣ ባለመድገምና የቀጣዩ ጊዜ ጀግና ትውልድ ሆነው ብልጽግናን ማረጋገጥ አለባችሁ” ሲሉም አስገንዝበዋል።

በሚኒስቴር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስተባባሪና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ክቡር አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ ለተመራቂ ተማሪዎችና ቤተሰቦች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ ተማሪዎች በአዲስ ተቋም ውስጥ ውጣ ውረድን አልፈው ለዚህ በመብቃታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

የኮቪድን ተጽዕኖ ተቋቁማችሁ ለዚህ ስኬት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ድግሪ ባስመረቃቸው ዕለት የተገኙት የእለቱ ክብር እንግዳ የሆኑት ክቡር አቶ ብናልፍ አንዷለም የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ርስቱ ይርዳውና የደቡብ ክልል ብልፅግና ፅቤት ሀላፊ ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ እና ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ከምርቃት ፕሮግራሙ በኋላም የቦንጋ የውሽ ውሽ ሻይ እርሻ ልማት ፣የዩኒቨርስቲው የልማት እና የምርምር ስራዎች፣ የጂማ አባጂፋር ቤተ መንግስት እንዲሁም የጅማ የከተማ River ኘሮጀክት ተጎብኝተዋል።

ምላሽ ይስጡ