You are currently viewing ፅንፈኛው የህወኃት ቡድን ለህግ እስኪቀርብ ድረስ ህግን የማስከበር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል-ክቡር አቶ ብናልፍ አንዷለም

ፅንፈኛው የህወኃት ቡድን ለህግ እስኪቀርብ ድረስ ህግን የማስከበር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል-ክቡር አቶ ብናልፍ አንዷለም

  • Post comments:0 Comments

ኢትዮጵያን ለማፈራረስ መከላከያን ማፍረስ የሚል ዓላማ ይዞ የተነሳውን ፅንፈኛው የህወኃት ቡድን ለህግ እስኪቀርብ ድረስ ህግን የማስከበር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ብናልፍ አንዷለም ተናገሩ፡፡“ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል በጽ/ቤቱ በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ብናልፍ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ግዳጁን እየተወጣ በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ጥቅምት 24 ምሽት በጁንታው የህወኃት ቡድን አስነዋሪ ጥቃት መፈጸሙን አውስተው በዓለም ታሪክ ለዓመታት የጠበቀውን የራሱ ሰራዊት ላይ ጥቃት የፈጸመ የእናት ጡት ነካሽ ቡድን ነውም ብለዋል፡፡ አቶ ብናልፍ በዛሬው መርሐ ግብር ላይ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ለሚገኘው ሰራዊታችን አጋርነታችንን የምናሳይበትና ክብር የምንሰጥበት እንዲሁም በህዝብና በመንግስት የተሰጣቸውን ግዳጅ ሲወጡ በጁንታው የህወኃት ቡድን ክህደት የተሰው የመከላከያ ሰራዊት አባላትንም የምንዘክርበት ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም ይህ እኩይ ድርጊት ከተፈጸመበት ጊዜ አንስቶ እስከአሁኑ ሰዓት ድረስ ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከዳር እያወገዙት መሆኑንና ይህ ቡድን ለፍርድ እስኪቀርብ ድረስ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡በመርሐ ግብሩ ላይ የጽ/ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች ተገኝተው ለሰራዊቱ ያላቸውን አጋርነትና ክብር አሳይተዋል፡፡

ምላሽ ይስጡ