You are currently viewing የርዕዮተ ዓለም እርግማን (ideology curse)

የርዕዮተ ዓለም እርግማን (ideology curse)

  • Post comments:0 Comments

ሁሉም ነገር ከአገርና ከህዝብ በታች ነው በሚል ጭንብል የሚመራው አብዮታዊ ዴሞክራሲ በከፋ የርዕዮተ ዓለም እርግማን ውስጥ እንዳለ ከትግራይ አሁናዊ ሁኔታ ውጭ ጥሩ ማሳያ የለም። አብዛኛው የትግራይ ወጣቶች የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ርዕዮተ-አለማዊ እርግማን የሚያሰቃያቸው እንደሆኑ በትህነግ ግፊት የተጀመረው ጦርነት ሁነኛ ማሳያ ነው። ትህነግ ጦርነቱን የጀመረው የትግራይ ምስኪን ወጣቶችን ህይወት አስይዞ ነው።የትህነግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ባለፉት ሰላሳ አመታት ምትሀታዊ በሆነ የዘረፋ ስልት ድንገታዊ ቱባ ባለሀብቶችን በአንድ ለሊት (Over night) እንደአሸን ፈልፍለዋል። ብልጽግናውን ለዘመዶቻቸውና ለቅርብ ጓደኞቻቸው አከፋፍለዋል። በጭንቅ ጊዜ ወደእሳት የማገዱት ግን የርዕዮተ አለም ተጠቂ የሆነውን ምስኪን የትግራይ ወጣት ነው። የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ርዕዮተ ዓለም እርግማን ሰለባዎችን በመተማመን የተጀመረው ጦርነት በግፉአን የኃይል የበላይነት ያለጥርጥር ይደመደማል። የሚያሳዝነውም የሚያሳቅቀውም የትግራይ ወጣት ልዩ ኃይል የተሰጠውን የሦሥት ቀን የሰላም አማራጭ ባለመቀበል በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ርዕዮተ-አለም እርግማን እየተገፋ ለወንበዴው ቡድን ጣኦት ጭዳ ሆኖ ማለቁ ነው።

ድል ለግፉአን !

ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት

ለጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል

ለጀግናው የአማራ ሚሊሻ ክብር እቆማለሁ !!!

አቶ አብርሃም አለኸኝ የብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

ምላሽ ይስጡ