You are currently viewing ሜ/ጄ መሀመድ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ጥሪ ስንቀበል ለሀገራችን ሉዓላዊነትና ለህዝባችን ክብር የማንከፍለው መስዋዕትነት እንደሌለ ዳግም በማረጋገጥ ነው ሲሉ ተናገሩ

ሜ/ጄ መሀመድ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ጥሪ ስንቀበል ለሀገራችን ሉዓላዊነትና ለህዝባችን ክብር የማንከፍለው መስዋዕትነት እንደሌለ ዳግም በማረጋገጥ ነው ሲሉ ተናገሩ

  • Post comments:0 Comments

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጄ መሀመድ ተሰማ፣ ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ!! የሚለውን የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ጥሪ ስንቀበል፣ ለሀገራችን ሉዓላዊነትና ለህዝባችን ክብር የማንከፍለው መስዋዕትነት እንደሌለ ዳግም በማረጋገጥ ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡በኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተነሳሽነትና አዘጋጅነት በነገው ዕለት ለሚደረገው ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ ጥሪ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ከፍተኛ ሞራልና ስንቅ እንደሚሆነውና ህዝብና መንግስት የሰጡትን ግዳጆች በከፍተኛ ተነሳሽነት በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ሰራዊቱም ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው፣ ህዝቡም በሙሉ አቅሙ ወደ ልማቱ እንደሚመለስ ገልጸዋል፡፡መርሐ ግብሩ በአዲስ አበባ የከተማው መስተዳድርና የከተማው ነዋሪዎች በጋራ የሚያከብሩት ሲሆን፣ ሰራዊቱና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችም በጋራ ያስቡታል፡፡በመርሐ ግብሩ ህግ ለማስከበር ተሰማርቶ ከፍተኛ ድሎችን እያስመዘገበ ለሚገኘው ጀግናው ሰራዊት ክብር የሚሰጠውና ህዝብና መንግስት የሰጣቸውን ግዳጅ ሲወጡ በከሀዲው ኃይሎች ክህደት የተሰው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት አባላትም ይዘከራሉ ብለዋል፡፡ፕሮግራሙን ሁሉም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ባሉበት የሚያከብሩት ሲሆን፣ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭትም እንደሚተላለፍ ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምላሽ ይስጡ