ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው።
ውይይቱ በመንግሥት እና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያሉ ወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል።
በውይይቱ በሰባት አጀንዳዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን፣ በቅድሚያ ግን ውይይት የሚደረግባቸው አራት አጀንዳዎች ተለይተዋል።
በቅድሚያ ሀገራዊ መግባባት ላይ ውይይት ለማድረግ የተስማሙ ሲሆን፣ በዚህም ጉዳይ ላይ ገለጻ ለማድረግ እና ለማወያየት ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሰዎች ተመርጠዋል።
በውይይቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ባንዳዎች የነበሩ ቢሆንም፣ እሱን ተቋቁመን ያቀድነውን አሳክተናል ብለዋል።
በቀጣይም ሀገራዊ ምርጫን በሚመለከት ከዚህ በፊት ከተደረው ምክክር የቀጠለ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።