Prosperity Party

ፓርቲዉ በወሰደዉ ቁርጠኝነት ክልሉ በአጭር ጊዜ የብልጽግና ተምሳሌት መሆን ችሏል- አቶ አደም ፋራህ

በብልፅግና ፓርቲ 2018 በጀት ዓመት 6 ወራት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና /ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እንደገለጹት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሁለት ዓመት ከአምስት ወራት የምስረታ ታሪክ ተምሳሌት የሆነ ዉጤት ማስመዝገብ የቻለዉ ፓርቲዉ በወሰደዉ ቁርጠኛ አቋም ነዉ፡፡

የተቋማትን ዝግጁነት በቅንጅት መምራት፣  ያለምንም የሰላምና የጸጥታ ችግር ወደ ስራ መግባት፣ መደበኛ አገልግሎቶች ሳይቆራረጡ መቀጠላቸዉ፣ ክልሉ በፋይናንስ ራሱን መቻሉ፣ ፈጥኖ ወደ ስራ መግባትና የማስፈጸም አቅም መገንባት መቻሉ አሁን ለተመዘገቡ ስኬቶች መሰረት መሆናቸዉን አብራርተዋል፡፡

ብልፅግና ፓርቲ ሁሉን አቃፊና ሁሉን አሳታፊ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ መሆኑን የተናገሩት አቶ አደም ፋራህ  በሙሉ እይታና በጥራት የመደመር ዕሳቤን መሰረት በማድረግ  አሰባሳቢ ትርክት መፍጠር መቻሉን  ገልጸዋል፡፡

ሁሉን አባላት ማብቃትና ብቁ አደረጃጀት መፍጠር ያለዉን ፋይዳ በመረዳት ለዚህ ስኬት በትኩረት ተሰርቷል ዉጤትም ተገኝቶበታል ብለዋል፡፡

በየደረጃዉ ብቁ የሆኑ ስትራቴጂያዊ አመራሮችን ለማፍራት በርካታ ስልጠናዎችን በመስጠት ሀገራዊ ለዉጡን መሸከምና ማስቀጠል የቻለ አመራር መፍጠር እንደተቻለ አንስተዋል፡፡

እንደ ፓርቲ በሁሉም መስኮች በተመዘገቡ ስኬቶችና ድሎች የህዝብ ቅቡልነት ማረጋገጥ እንደተቻለ ያብራሩት አቶ አደም ወጥነት ያለዉ ተቋማዊ ስርዓት መዘርጋት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡

የአመራሩንና የአባሉን አቅም በስልጠና በመገንባት ወጥነት ያለዉን ተቋማዊ አሰራር መዘርጋት ተችሏል ብለዋል፡፡

ዲጂታል ኢትዮጵያ እዉን ለማድረግ በሚደረግ ጥረት ዉስጥ እንደ ፓርቲ አርዓያ ለመሆን ዲጂታል ብልጽግናን ማረጋገጥ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ 

በግምገማ መድረኩ በፓርቲ ስራዎች ባለፉት ስድስት ወራት በተመዘገቡ ስኬቶችና ዉስንነቶች እንዲሁም በቀጣይነት ትኩረት በሚያስፈልጉ ጉዳዮች  ላይ በስፋት ዉይይት እየተደረገ ነዉ፡፡

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party