ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጣሊያን የሚኒስትሮች ም/ቤት ፕሬዝዳንት አቀባበል አደረጉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሁለተኛው የጣሊያን-አፍሪካ ጉባዔ ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የጣሊያን ሪፐብሊክ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጆርጂያ ሜሎኒን ተቀብለዋል።
ይህንን አስመልክተዉም በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት "ጉባኤው በኢትዮጵያና ጣሊያን መካከል ያለውን ጠንካራና እያደገ የመጣውን አጋርነት የሚያንጸባርቅ ሲሆን፣ ይህም ሁለቱ ሀገራት በጣሊያን እና በአፍሪካ መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግ ያላቸውን አጋርነት ያሳዬ ነው" ብለዋል።