የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ካቀረቧቸዉ ጥያቄዎች መካከል:-
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካነሷቸው ጥያቄዎች፡-
⨳የፍትህ ዘርፉን በተመለከት የፍትህ ዘርፉ አሁንም ለውጥን የሚሻ ነው ምን እየተሰራ ነው?
⨳የመሰረተ ልማት ስራዎች ቤንሻንጉል ላይ የለም በቀጣይ ምን ታስቧል?
⨳መንግስት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን ስራዎችን እየሰራ ነው ሆኖም በአንዳንድ ተቋማት ላይ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ይስተዋላሉ መንግስት ምን አስቧል?
⨳ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ቅድምያ የመስጠት የዲፕሎማሲ ስራ ላይ በንቃት እየሰራች ነው በአጠቃላይ አሁን ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለን ግንኙነት ምን ላይ ነው?
⨳ተዳክሞ የቆየው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄው አንዳንድ ኢትዮጵያን የሚጎዱ መረጃዎች እየወጡ ይገኛል እሱ ላይ ምን እየተሰራ ነው?
የዲፕሎማሲው ሂደትስ ምን ላይ ደርሷል?