Prosperity Party

ኢቢሲ በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የራሱን አሻራ ያኖረ ትልቅ ተቋም ነው፡ - ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)

 

ኢቢሲ ኢትዮጵያን በመገንባት እና አንድነቷን በማጠናከር በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የራሱን አሻራ ያኖረ ትልቅ ተቋም ነው ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድ ካቲንግ ኮርፖሬሽን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ታርጫ ከተማ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ የሆነውን አዲስ ስቱዲዮ በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እንደ ኢቢሲ አይነት ዕድሜ ጠገብ ተቋማት ኢትዮጵያን በመገንነባት ሂደት ውስጥ ጠንካራ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የተጋመደ ጉዞ መገለጫው የተቋማት ግንባታ ነው ያሉት ዶክተር ቢቂላ፤ እንደ ኢቢሲ ያሉ አንጋፋና ጉምቱ ተቋማት ኢትዮጵያውያንን እያጋመዱ፣ ወንድማማችነትን እያጠናከሩ፣ ቂምና ቁርሾን ሳይሆን ፍቅርን እየሰበኩ ለሀገር ግንባታ የራሳቸውን አሻራ አኑረው እዚህ ደርሰዋል ብለዋል፡፡

ኢቢሲ አንድነትን፣ አብሮነትን እንዲሁም የትስስር ታሪኮችን እየገነባ የመጣ ተቋም ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

'ኢቢሲ ወደ ይዘት' በሚል መሪ ቃል ተጨማሪ ይዘቶችን ለማመንጨት ወደ ህብረተሰቡ ወርዶ የህብረተሰቡን ባህል፣ ቋንቋ እንዲሁም ፍላጎት በሚገባ ለመረዳት በሚየያስችል ሁኔታ በመስራት በተግባር እያሳየ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party